category stringclasses 4
values | headline stringlengths 17 80 | text stringlengths 1 16.8k | url stringlengths 36 49 |
|---|---|---|---|
business | አውስትራሊያ ፡ የሒትለርን ቪዲዮ በመጠቀም ፌስቡክ ላይ በአለቆቹ የተሳለቀው ሠራተኛ 200 ሺህ ዶላር ተሰጠው | ስኮት ትሬሲ ይባላል፡፡ የግዙፉ የብሪቲሽ ፔትሮሊየም ኩባንያ (ቢፒ) ሠራተኛው ነበር፡፡ የዛሬ ሁለት ዓመት ከዕለታት በአንዱ ከሥራ ይባረራል፡፡ የተባረረው አርፍዶ ሥራ በመግባቱ ወይም እንዝህላል ሆኖ አይደለም፡፡ የገዛ መሥሪያ ቤቱ ላይ በመሳለቁ እንጂ፡፡ የተሳለቀበት መንገድ ግን ሳያስበው ዝነኛ አድርጎታል፡፡ ሰውየው በፌስቡክ ለቅርብ ጓደኞቹ አንድ ቪዲዮ ያጋራል፡፡ ቪዲዮው የተወሰደው 2004 ዓ.ም ላይ ዝነኛ ከነበረው ዳውንፎል (Downfall) የሆሊውድ ፊልም ላይ የተቀናበረ ነው፡፡ በመሥሪያ ቤቱ ውስጥ ... | https://www.bbc.com/amharic/news-53732694 |
health | ኤርትራውያን በካንሰር ለሚሰቃይ ግለሰብ በ24 ሰዓታት ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን ዶላር አሰባሰቡ | በውጭ አገራት የሚኖሩ ኤርትራውያን እና ትውልደ ኤርትራውያን ዲያስፖራዎች በሕመም ለሚሳቃይ አንድ ኤርትራዊ ግለሰብ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን የካናዳ ዶላር በላይ አሰባሰቡ። በኤርትራ ነዋሪ የሆነው እና የስድስት ልጆች አባት የሆነው ዮናስ ፀጋይ፤ ባለፈው አንድ ዓመት ሆድኪን ሊምፎማ በተባለ የደም ካንሰር አይነት ሲሰቃይ ቆይቷል። 'ዮናስ ፀጋይን እና ቤተሰቡን ይርዱ' በሚል በተከፈተው የጎፈንድሚ አካውንት በ24 ሰዓታት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የካናዳ ዶላር ማሰባሰብ ተችሏል። ለዮናስ የተሰባሰ... | https://www.bbc.com/amharic/news-60041868 |
business | ኤለን መስክ የማይክሮሶፍቱን ቢል ጌትስን በልጦ የዓለማችን 2ኛው ቢሊየነር ሆነ | የቴክኖሎጂ ፈጣሪው ኤለን መስክ በአጭር ጊዜ ውስጥ የዓለማችን 2ኛው ቢሊየነር ሆነ። መስክ የማይክሮሶፍቱን ቢል ጌትስን በልጦ ነው እዚህ ደረጃ ላይ የተቀመጠው። የኤለን መስክ ሀብት በአጭር ጊዜ የተምዘገዘገው ቴስላ የተባለው የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ኩባንያው በስቶክ ገበያ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ተከትሎ ነው። ይህ ድንገተኛ የሀብት ጭማሪ የኤለን መስክን የሀብት መጠን ከ7 ቢሊዮን ወደ 128 ቢሊዮን አድርሶታል። የቢሊየነሮችን ዝርዝር የሚያስቀምጠው ብሉምበርግ እንደሚለው ከሆነ በዚህ ሰዓት ኤለን መስክ... | https://www.bbc.com/amharic/55056387 |
health | እንቅልፍ በመቀነስ የሥራ ጫናን ‘የመበቀል’ ልማድ | ማ ራዎ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት፤ በሳምንት ለስድስት ቀናት ትሠራ ነበር። ቻይና፣ ሻንጋይ ውስጥ ለሚገኝ መድኃኒት አምራች ትሠራ የነበረው ማ፤ በአጭር ጊዜ ነበር ሕይወቷ በሥራ የተዋጠው። ለመመገብ አጭር ሰዓት ብቻ ነበራት። ለመተኛትም እንዲሁ። "ከሥራ ውጪ ምንም የግል ሕይወት አልነበረኝም። ድብርት ይዞኝ ነበር" ትላለች። ሥራዋ ለግል ሕይወት ጊዜ ስላሳጥት እንቅልፏን መስዋዕት እያደረገች ለራሷ ጊዜ ለመስጠት ትሞክር ነበር። ካላት አጭር የመኝታ ጊዜ ቀንሳ ዜና ማንበብ፣ ቪድዮ ማየት ጀመረች።... | https://www.bbc.com/amharic/news-56051981 |
sports | ኳታር ለዓለም ዋንጫ እንዴት ተመረጠች፣ ውድድሩ ለምን ኅዳር ላይ ሆነ? | ሚሊዮኖች. . . ቢሊዮኖችም ሊሆን ይችላል፤ በጉጉት የሚጠብቁት የዓለም እግር ኳስ ፍልሚያ በቀጣይ ዓመት ኅዳር ላይ መካሄድ ይጀምራል። የዓለም ዋንጫ ውድድር ኅዳር ወር ላይ ሲሆን ይህ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። አዘጋጇ ደግሞ የመካከለኛ ምሥራቋ ቱጃር አገር ኳታር ናት። የዓለም ዋንጫ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሲያመራም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። አስካሁን ከሁለት አገራት በስተቀር በዚህ ተወዳጅ ፍልሚያ ላይ መሳተፋቸውን አረጋግጠዋል። ሁለቱ አገራት ደግሞ በዚህ ሳምንት በሚደረገው ኢንተርኮንቲኔንታል ጥሎ ማለፍ ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/c51wglqrq46o |
business | ከኑሮ ውድነት ጋር ግብ ግብ የገጠሙት የመንግሥት ሠራተኞች | ረድኤት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኝ የሥራ እድል ፈጠራ ጽህፈት ቤት ውስጥ ሠራተኛ ነች። በዚህ ዘገባ ውስጥ የተካተቱ ሁለቱም የመንግሥት ሠራተኞች ስማቸው ተቀይሯል። ሥራቸውን እንዳያጡ ሰግተዋል። ትውልድ እና እድገቷ አዲስ አበባ ነው። "ከቤተሰቤ ጋር ባይሆን በ 2700 ብር ደሞዝ ተቀጥሬ እንዴት እኖር ነበር?" ስትል ከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት የነበራትን የመነሻ ደመወዝ ትናገራለች። አሁን እንደምንም አምስት ሺህ ብር ይደርሳታል። በቅርቡ ትዳር ይዛ ከቤተሰቦቿ ቤት የወጣችው ረድኤት የቤት ... | https://www.bbc.com/amharic/news-58215116 |
politics | ባልደራስ አቶ እስክንድር ነጋ በእስር ቤት 'የደኅንነት ስጋት ገጥሞታል' አለ | አዲስ አበባ በሚገኝ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፕሬዘዳንት አቶ እስክንድር ነጋ "ደኅንነታቸው አደጋ ላይ ወድቋል" ሲል ፓርቲያቸው ስጋቱን ገለጸ። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ገለታው ዘለቀ፤ አቶ እስክንድር ቃሊቲ ከሚገኘውና በተለምዶው 'ዋይታ' ተብሎ ከሚጠራው የማረሚያ ቤቱ ክፍል ወይም ዞን ወደ ሌላ እንዲዘዋወሩ በመደረጉ ስጋቱ መፈጠሩን ለቢቢሲ ገልጸዋል። አቶ ገለታው በስም ያልጠቀሷቸው "ከእስር ቤቱ ውጪ ያሉ" ባሏቸው ወገኖች... | https://www.bbc.com/amharic/news-57397740 |
sports | ኢንተር ሚላን የማንችስተር ዩናይትዱን ጄሲ ሊንጋርድ ለማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ተነገረ | በዘንድሮው የጥር የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ክለቦች የሚያተኩሩባቸውን ተጫዋቾች እየጠቀሱ ነው። ምንም እንኳ እስካሁን በዝውውሩ ስማቸው የሚነሳ ትልልቅ ተጫዋቾች ቁጥር አናሳ ቢሆንም በርከት ያሉ ተጫዋቾች ግን በዝውውሩ ክለብ የቀይራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የጣሊያኑ ክለብ ኢንተር ሚላን፤ የማንችስተር ዩናይትድና የአንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የሆነውን የ28 ዓመቱን ጄሲ ሊንጋርድን ለመውሰድ ፍላጎት ማሳየቱን ሚረር ዘግቧል። ይህ የሚሆነው ግን ኢንተር ሚላን ዴንማርካዊው ክርስቲያን ኤሪክሰንን ካሰናበተ ነው ተ... | https://www.bbc.com/amharic/news-55608009 |
health | “እስክሞት ልታገል”፡ የኩላሊት ህሙማን መርጃ ያቋቋመው የኩላሊት ታማሚ | የህክምና ምርመራ ውጤት! ሕይወታችንን ባላሰብነው፣ ባልጠበቅነው መንገድ ይገለባብጣል። ለኢዮብ ተወልደመድኅን ያ ክፉ ጊዜ ጥቅምት 2006 ዓ.ም ነበር። የኩላሊት ታማሚ እንደሆነ ሐኪሞች ሲገሩት። የሁለት ሴት ልጆች አባት የሆነው ኢዮብ ይህን ዜና ሲሰማ የሚገባበት ጠፋው። ባለቤቱ በድንጋጤ ከፍተኛ ሐዘን ተጫናት። አዲስ አበባ ውስጥ የተክለሐይማኖት ሰፈር ልጅ ነው። ከ1979 ዓ. ም. ጀምሮ ግን ለአምስት ዓመታት አሰበ ተፈሪ ኖሯል። ዘጠነኛ ክፍልን አብዮት ቅርስ ትምህርት ቤት ተምሮ 10ኛ ክፍል ጥቁር አንበሳ... | https://www.bbc.com/amharic/news-58126744 |
health | ኮሮናቫይረስ፡ በካናዳ አንዲት ጨቅላ ሕጻን ጭምብል ባለማጥለቋ በረራ ተሰረዘ | ነገሩ አስገራሚ ነው፡፡ በካናዳ አንዲት ጨቅላ ሕጻን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ባለማድረጓ ብቻ ፖሊስ ተጠርቷል፣ በረራውም ተሰርዟል፡፡ ሕጻኗ ከተወለደች ገና 19 ወሯ ነው፡፡ ዌስት ጄት ደግሞ ሁሉም ተሳፋሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማጥለቅ እንዳለባቸው ያሳስባል፡፡ ጨቅላዋ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሲደረግላት እሪታዋን ታቀልጠዋለች፡፡ ብትባል ብትሰራ እምቢኝ ትላለች፡፡ እናትና አባት ያልሞከሩት ነገር የለም፡፡ ሕጻኗ ሞቼ እገኛለሁ አለች፡፡ የአየር መንገዱ አስተናጋጆችና ቤተሰብ አንድ ሁለት ሲባባሉ ነገሩ ተካሮ... | https://www.bbc.com/amharic/news-54098154 |
sports | አትሌቲክስ ፌደሬሽን፡ 'በኦሊምፒክ የሚሳተፉ ሯⶐች የሚመረጡት በቴክኒክ ኮሚቴ ነው' አለ | በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው በማራቶን የሚወደዳሩ አትሌቶችን የሚመርጠው ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ እንዲሆን ከስምምነት መደረሱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ። ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ በኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝደንት በሆኑት አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የሚመራ ሲሆን የአትሌቲክስ አሰልጣኞች የኮሚቴው አባላት ናቸው። ይህንን በሚመለከት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛሬ ማክሰኞ መግለጫ ሰጥቷል። የዛሬው መግለጫ የአትሌቲክ ፌዴሬሽን፣ የኦሊምፒክ፣ የፌደራል ስፖርት ኮሚሽን እና ባህል እና ቱሪዝ... | https://www.bbc.com/amharic/news-57076979 |
business | ባይደን ለችግር ጊዜ ከተከማቸው ነዳጅ በርካታ ሚሊዮን በርሜል እንዲቀዳ አዘዙ | የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አሜሪካ ለችግር ጊዜ በሚል ካከመቻችው ነዳጅ በገፍ እንዲቀዳ አዘዋል። ፕሬዝደንቱ ይህን ትዕዛዝ ያስተላለፉት እየናረ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ ለመዋጋት ነው። ባይደን እንዲወጣ ያዘዙት 180 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ በማከማቻው ታሪክ ትልቁ ነው። ዩክሬን ባለው ጦርነት ምክንያት ጣራ እየነካ የነበረው የነዳጅ ዋጋ ከባይደን ትዕዛዝ በኋላ ትንሽ ረገብ ብሏል። ነገር ግን አሜሪካ በየቀኑ ለመከራ ጊዜ ካስቀመጠችው ነዳጅ አንድ ሚሊዮን በርሜል ብትቀዳም ችግሩን ሙሉ በሙሉ አይቀርፈ... | https://www.bbc.com/amharic/news-60950886 |
politics | በሆሮ ጉድሩ በታጣቂዎች የተገደሉ ሰላማዊ ነዋሪዎች ከ100 በላይ እንደሆኑ ኢሰመኮ ገለጸ | በባለፉት ሳምንታት በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በታጣቂዎች የተገደሉ ሰላማዊ ነዋሪዎች ከ100 በላይ እንደሆኑ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። በሰላማዊነዋሪዎች ላይ ግድያውን የፈጸሙት መንግሥት ሸኔ ብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት፣ የአማራ ኢመደበኛ ታጣቂ ኃይሎችና ግለሰቦች ባደረሱት ተከታታይ ጥቃት መሆኑንም ኢሰመኮ በትናንትናው ዕለት መስከረም 16፣ 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። በዞኑ ኡሙሩ፣ ሆሮ ቡልቅ እና ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳዎች ከነሐሴ 25 ቀን 2014ዓ.ም ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/c2q4ex3k0n1o |
sports | በኮቪድ ምክንያት 11 ተጫዋቾች እንኳን ቢቀሩ ጨዋታ እንደማይሰረዝ ካፍ ገለጸ | በአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፉ ሃገራት የኮቪድ1-9 ወረርሽኝ ቢያጋጥማቸውና 11 ተጫዋች ብቻ ቢቀራቸው እንኳ ጨዋታው እንደማይሰረዝ ካፍ ገልጿል። የአፍሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪው ካፍ ከአስራ አንዱ ተጫዋቾች አንዱም ግብ ጠባቂ ባይሆን ጨዋታው እንደማይሰረዝ አስታውቋል። ይህንን ማሟላት የማይችል ቡድን በተለምዶ ፎርፌ በሚባለው ሕግ መሠረት የ2-0 ሽንፈት ይጣልበታል ይላል ካፍ። ካፍ ይህንን ትዕዛዝ ያስተላለፈው ዛሬ ምሽት [እሑድ] ከሚጀምረው ውድድር በፊት በርካታ ሃገራት ተጫዋቾቻችን በኮቪድ ተይዘዋል ብለው ካማ... | https://www.bbc.com/amharic/news-59926712 |
sports | አርሰናል 5 ሲያስቆጥር፤ ዩናይትድ በዴ ሂያ ጥረት 3 ነጥብ ይዞ ወጥቷል | ትናንት በተከናወኑ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች አርሰናል እና ማንችስተር ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል። አርሰናል በኢሚሬትስ ስታዲየም በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ መጨረሻ ላይ የሚገኙትን ኖቲንግሃም ፎረስተን አስተናግደው አምስት ጎሎዎችን አከናንበዋቸዋል። ገብርኤል ማርቲኔሊ፣ ሪስ ኔልሰን፣ ቶማስ ፓርቴ እና ማርቲን ኦዴጋርስ ለአርሰናል ጎል ያስቆጠሩ ተጨዋቾች ናቸው። መድፈኞቹ በድንቅ የጨዋታ ብቃት ያገኙት ሦስት ነጥብ በ31 ነጥቦች በሊጉ መሪነት እንዲቀጥሉ አስቸሏቸዋል። የመጀረሚያውን ጎል ለገርኤል ማርቲኔ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2nk0077d3o |
politics | ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ምክክሩ ስኬታማ እንዲሆን ሒደቱ ተቀባይነት ያለው መሆን አለበት አሉ | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “አካታች ብሔራዊ ምክክሩ” ስኬታማ እንዲሆን ሒደቱ ተቀባይነት ያለው ሆኖ መከናወን አለበት አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ መጋቢት 23/2014 ባወጡት መግለጫ ብሔራዊ ምክክሩ የፖለቲካ ፈተናዎቻችንን መቅረፍ የሚያስችለን ወርቃማ እድል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ብለዋል። “ይህን ወርቅ የሆነ አጋጣሚ . . . እንደ ዕንቁ አክብረንና ተከባክበን ከተጠቀምንበት ዋጋው ከፍ ያለና ታሪክ ቀያሪ ዕድል ይሆናል” ብለዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ማድረግና ... | https://www.bbc.com/amharic/news-60954318 |
business | ቱርክ፡ ፕሬዝደንቱ የማዕከላዊ ባንክ ገዢውን ካባረሩ በኋላ የሃገሪቱ ገንዘብ 14 በመቶ ላሸቀ | የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን የሃገሪቱን ማዕከላዊ ባንክ አስተዳደሪ ማበረራቸውን ተከትሎ የቱርክ መገበያየ ሊራ 14 በመቶ ላሸቀ። የቀድሞ የባንክ ገዢ ናሲ አግባል፤ ሊራ በጣም ዘቅጦ ከነበረበት ከፍ አድርገው ለዚህ ያበቁ ሰው ናቸው የሚል ሙገሳ ይቸራቸዋል። ነገር ግን ፕሬዝደንት ኤርዶዋን ሳይታሰብ ባለፈው ቅዳሜ ሰውዬውን አንስተው በሌላ ተክተዋቸዋል። ቱርክ የማዕከላዊ ባንክ አስተዳዳሪ ስታባርር በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይህ ሶስተኛው ነው። ባለፈው ኅዳር የተሾሙት አግባል ከ15 በመቶ በላይ እየ... | https://www.bbc.com/amharic/news-56480620 |
health | የጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ወደ ውጪ የሚደረገውን ጉዞ ያስቀር ይሆን? | የሰበታ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ አሕመድ አባዲ የሦስት ዓመት ልጃቸው በጭንቅላት ካንሰር በመታመሙ ከሰባት ወራት በፊት ታይላንድ ባንግኮክ ከተማ ወስደው አሳክመዋል። “ከዚያ ተመልሰን በሦስተኛው ወር ስናስመረምረው በአከርካሪ አጥንቱ ላይ ካንሰር ተገኘበት” ይላሉ አቶ አሕመድ። የልጃቸው የጤና በጣም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደነበር የሚናገሩት አቶ አህመድ፣ “መቀመጥ፣ መሄድ፣ መተኛት እና ምግብ መዋጥም አይችልም ነበር” ይላሉ። በዚህ ሰዓት ነበር አቶ አሕመድ ልጃቸውን እና ቤተሰባቸውን ይዘው ወደ ጅማ ከተ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cx80yr27ezqo |
health | ኮሮረናቫይረስ፡ ጃፓናዊቷ የኮቪድ-19 ታማሚ በህይወት ካለ ሰው የሳንባ ንቅለ ተከላ በማድረግ የመጀመሪያ ሆነች | አንዲት የኮቪድ-19 ታማሚ ጃፓናዊት በህይወት ካሉ ሰዎች ሳንባ በመቀበል በዓለማችን የመጀመሪያዋ የኮሮናቫይረስ ህመምተኛ ለመሆን በቃች። ግለሰቧ በቀዶ ህክምና በአካሏ ላይ እንዲገባ የተደረገውን የሳንባ ክፍል ከልጇና ከባሏ የተበረከተ ነው ተብሏል። ታማሚዋ ሳንባው የተለገሳት በኮሮናቫይረስ ምክንያት የመተንፈሻ አካሏ እንደ አንድ የሰውነት ክፍሏ መደበኛውን ሥራውን መሥራት በማቆሙ ነው። በኪዮቶ የሚገኙ ሐኪሞች እንዳሉት ሴትየዋ በቅርብ ወራት ውስጥ አገግማ ወደ ሙሉ ጤናዋ ትመለሳለች። ጃፓን ውስጥ ከሞቱ ሰዎች... | https://www.bbc.com/amharic/news-56674361 |
politics | የአፍሪካ አገራት መሪዎች በመንግሥት ምስረታ በዓለ ሲመት ላይ ምን አሉ? | ዛሬ መስከረም 24/2014 ዓ.ም እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ አዲስ መንግሥት መስረታ በዓለ ሲመት ላይ የተገኙ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ንግግር አድርገው ለኢትዮጵያና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ባለው የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በዓለ ሲመት ሥነ ሥርዓት ላይ የተጋበዙት የኡጋንዳው ፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ፤ በኡጋንዳ ሕዝብ ስም የኢትዮጵያን ሕዝብ እና ጠቅላይ ሚንስትሩን "እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል። በኡጋንዳ የጎሳ እና የሃይማኖት ክፍፍል ... | https://www.bbc.com/amharic/news-58792454 |
business | ከጉሊት እስከ ቅንጡ ሆቴል ግብይትን ያሳለጠው ኤም-ፔሳ ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣል? | ከሁለት ወራት በኋላ በኢትዮጵያ ሥራ እንደሚጀምር ያስታወቀው ሳፋሪኮም፤ ኤም-ፔሳ የተባለውን የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት በአገሪቱ እንዲዘረጋ መንግሥት ፍላጎት እንዳለው ተዘግቧል። የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝን ጠቅሰው የአገር ውስጥ እና የኬንያ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ሳፋሪኮም ኤም-ፔሳን ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲጀምር ይፈልጋል። ከዚህ ቀደም መንግሥት የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓትን ለውጭ አገራት ኩባንያዎች ክፍት... | https://www.bbc.com/amharic/60329210 |
politics | ኬንያ ከሰሃራዊ አረብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጋር ግንኙነቷን ማቋረጧን አስታወቀች | ከተሾሙ ቀናትን ያስቆጠሩት የኬንያው ፕሬዘዳንት ዊልያም ሩቶ አገራቸው ከሰሃራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ (ሳዲአር)ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን ገለጹ። ፕሬዚዳንቱ ትላንት ረቡዕ በትዊተር ገጻቸው ላይ ይህንኑ መልዕክት አስፍረው የነበረ ሲሆን ከሰአታት በኋላ ግን ልጥፉን አንስተዋል። የቀድሞ የስፔን ቅኝ ግዛት የነበረው ይህ የምዕራብ ሰሃራ አካባቢ እ.ኤ.አ በ1975 ከቅኝ ግዛት ከተላቀቀ በኋላ ሞሮኮ ግዛቴ ነው በሚል በቁጥጥሯ ስር ለማድረግ ሙከራዎችን አድርጋለች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የሰሃራዊ ነባር ሕብ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cn3rvr7v2e2o |
politics | ከሰሞኑ የጋምቤላ ጥቃት ጀርባ ያለው ቡድን ማን ነው? | ማክሰኞ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም ማለዳ ላይ የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት-ሸኔ በጋራ በመሆን በጋምቤላ ከተማ ላይ ጥቃት በመክፈት ከተማዋ ለቀናት ከተለመደ እንቅስቃሴዋ ውጪ ሆና ቆይታለች። የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ጋትሉክ ቡኦም ፓል ጥቃታቸው የጀመረው ከከተማው 4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ደምቢዶሎ መውጫ ላይ ከሚገኝ ጫካ በመነሳት እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለተወሰኑ ሰዓታት በርካታ የከተማዋን ክፍሎች ተቆጣጥረው እንደነበር የሚናገሩት ሊቀመንበሩ ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2mp4jrdzmo |
business | የምዕራባውያንን ማዕቀብ ለሚሸሹት ሩሲያውያን መሸሸጊያ የሆነችው ዱባይ | የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ ከቭላድሚር ፑቲን አስተዳደር ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ የሩሲያ ባለጸጎች ከምዕራባውያን ማዕቀበ ለማምለጥ ዱባይን መዳረሻቸው እያደረጉ ነው። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቢሊየነር ሩሲያዊያን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትሷ ዱባይ እየገቡ ነው። አንድ ሪፖርት በመጀመሪያዎቹ የ2022 ሦስት ወራት ዱባይ ውስጥ በሩሲያ ባለሀብቶች የተገዙ ንብረቶች መጠን በ67 በመቶ ጨምሯል ብሏል። ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ እስካሁን ድረስ የዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ በሩሲያ ላይ ማዕ... | https://www.bbc.com/amharic/news-61330372 |
business | ባለፈው ዓመት ለኑሮ መወደድ ምክንያት የሆኑት ዋነኛ ክስተቶች የትኞቹ ናቸው? | ባለፈው ዓመት በዓለም ዙሪያ ከዚህ በፊት ከታየው በከፍተኛ ሁኔታ የናረ የምርት እና የአገልግሎቶች ዋጋ መናር ተከስቷል። ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች የሚቀርቡ ሲሆን፣ ይህ ቪዲዮ የዓለምን ሕዝብን ክፉኛ ላስጨነቀው የዋጋ ንረት ሰበብ ለሆኑት መካከል ዋናዎቹን ይዳስሳል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cgr0n57lp2xo |
health | ዋነኛ ምልክቱ የጀርባ ሕመም የሆነው የደም ካንሰር ዓይነት | መልቲፕል ማይሎማ (Multiple myeloma) የደም ሥርዓትን የሚያጠቃ እና በብዛት ያልተለመደ የደም ካንሰር ዓይነት ነው። በብዛት በኩላሊት እና በአጥንት ላይ የተለያዩ እክሎችን ያስከትላል። በዚህም የተነሳ የሕመም ምልክቶቹ ከሌላ ሕመም ለመለየት አስቸጋሪ ያደርገዋል። ይህ ሕመም በሽታ ተከላካይ የሆኑትን ነጭ የደም ህዋሳትን፣ ፕላዝማ ህዋሳትን ያጠቃል። እነዚህ የተጠቁ ህዋሳት ደግሞ የተበላሹ ህዋሳትን በመፈጠር እየተባዙ፣ ጤናማ ያልሆነ የሰውነት በሽታ ተከላካይ ህዋሳትን ያመርታሉ። ይህም ኤም ፕሮቲን (... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cw4pxx87kyeo |
sports | ሁለቱንም እጆቹን ያጣው ቻይናዊ አራት የፓራ ኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎችን ሰበሰበ | ቻይናዊው የፓራ ዋናተኛው ዤንግ ታኦ በቶኪዮ ፓራ ኦሎምፒክ አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ማሸነፉና ክብረ ወሰኖችን መስበሩ በርካቶችን እያስገረመ ይገኛል። ዤንግ አካል ጉዳተኛ ሲሆን ሁለቱንም እጀቹን አጥቷል። ''ልጄ ተመልከቺ፤ ምንም እንኳን እጆች ባይኖሩኝም በጣም ፈጣን ዋናተኛ ነኝ'' ብሏል ውድድሩን ካሸነፈ በኋላ ለሴት ልጁ በላከው የተንቀሳቃሽ ምስል መልዕክት። ዤንግ ገና ታዳጊ ሳለ ነበር በኤሌክትሪክ ሾክ ምክንያት ሁለቱንም እጆቹን ያጣው። በቶኪዮ ፓራ ኦሎምፒክ ድሞ በነጻ ቀዘፋ፣ ባክስትሮክ እንዲሁም በ... | https://www.bbc.com/amharic/news-58452725 |
politics | በሞቃዲሾ የተከሰተው ውጊያ የለየለት ጦርነት እንዳይቀሰቅስ አስግቷል | በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በሁለት ተጻራሪ ኃይሎች መካከል ውጊያ ተካሄደ። ትናንት እሁድ ከአገሪቱ ቤተ መንግሥቱት አቅራቢያ የከባባድ መሣሪያዎች ድምጽና የተኩስ ልውውጥ እንደነበረ ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች አመላክተዋል። ሞርታር ጭምር የፕሬዝዳንቱ መቀመጫ ወደሆነው ቤተ መንግሥት ስለመተኮሱ ተሰምቷል። ውጊያው ምናልባትም ፕሬዝዳንት ፋርማጆን በሚደግፉና በሚቃወሙ የሠራዊት አካላት አልያም በታጣቂዎች መካከል ሳይካሄድ እንዳልቀረ ተጠርጥሯል። ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ወይም (ይበልጥ... | https://www.bbc.com/amharic/news-56884281 |
health | ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በድጋሚ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆኑ | ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለማችንን ትልቁን የጤና ተቋም የዓለም የጤና ድርጅትን ለሁለተኛ ዙር እንዲመሩ ዳግም ተመረጡ። የዶ/ር ቴድሮስ ብቸኛ ዕጩ ሆነው ዳግም መመረጣቸው የተረጋገጠው በጄኔቫ ላይ እየተካሄደ በሚገኘው 75ኛው የዓለም ጤና ድርጅት ጠቅላላ ጉብዔ ላይ ነው። ዶክተር ቴድሮስ ያለተፎካካሪ በብቸኛ ዕጩነት በቀረቡበት መድረክ ላይ ከተለያዩ የድርጅቱ አባል አገራት ለዕጪነት ለተሰጣቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። የዋና ዳይሬክተሩ ምርጫን በመደገፍ በቦትሰዋናው ተወካይ በኩል የአፍሪካ አገራት ቡድንን... | https://www.bbc.com/amharic/news-61568901 |
health | በአሜሪካ ሲካሄድ የነበረ የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ተቋረጠ | ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ሲያካሂድ የነበረውን ምርምር አንድ በጎ ፍቃደኛ መታመሙን ተከትሎ ማቋረጡን አስታወቀ። ኩባንያው እንዳለው በክትባት ሙከራው ላይ እየተሳተፈ የነበረው በጎ ፍቃደኛ የጤና እክል የገጠመው ክትባት ለማግኘት ከሚደረገው ምርምር ጋር ተያይዞ ስለመሆኑ ይጣራል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በጎ ፍቃደኞች በሚሳተፉበት ምርምር ላይ በጎ ፍቃደኞች የጤና እክል ሊገጥማቸው እንደሚችል ኩባንያው አስታውሶ፤ ለጥንቃቄ ሲባል ሶስተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው የሙከራ ምርምሩ እንቋዲረ... | https://www.bbc.com/amharic/54526621 |
sports | የዓለማችን ኮከብ አትሌት ሞ ፋራህ ለዘመናት የደበቀውን ምስጢር ይፋ አወጣ | ከዓለማችን ኮከብ አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው ሞ ፋራህ በህፃንነቱ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም መወሰዱን እና ለአስገዳጅ የጉልበት ብዝበዛ መጋለጡን ይፋ አደረገ። በስፖርቱ ዘርፍ ለዩናይትድ ኪንግደም ባበረከተው አስተዋጽኦ በአገሪቱ ከፍተኛ ማዕረግ የሆነውን ‘ሰር’ የሚለውን መለያ ያገኘው ሞ ፋራህ ስሙ በወላጆቹ የተሰጠው ሳይሆን ሐሰተኛ ነው ብሏል። ፋራህ በህጻናት ላይ የሚደርሰውን የጉልበት ብዝባዛ ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት እውነተኛ ታሪኩን ይፋ በማውጣወት ያለፈበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ለ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cyrkz71kx1do |
health | የታንዛኒያው ፕሬዝደንት የኮቪድ-19 ክትባት ለታንዛኒያውያን አያስፈልግም አሉ | የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ የአገሪቱ ጤና ባለስልጣናት የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመጠቀም ከመወሰናቸው በፊት ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው አሉ። ማጉፉሊ ምንም አይነት ማረጋገጫ ሳያቀርቡ የኮቪድ-19 ክትባት ሕዝቡን ሊጎዳ ይችላል ብለዋል። "የጤና ሚንስቴር ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ጥናቶችን ሳያከናውኑ እነዚህን ክትባቶች ለመሞከር መፍጠን የለባቸውም። ሁሉም ክትባት ለእኛ ጠቃሚ አይደሉም፤ መጠንቀቅ አለብን። መሞከሪያ መሆን የለብንም" ሲሉ ማጉፉሊ ተናግረዋል። "ክትባቶች አደገኛ ናቸው። ነጩ ሰውዬ... | https://www.bbc.com/amharic/55825410 |
health | ሲዲሲ የኮቪድ-19 ክትባት የሚሰራጭበት መንገድ ላይ የአሜሪካ ግዛቶች ቀድመው እንዲዘጋጁ አሳሰበ | የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) የአሜሪካ ግዛቶች የጤና ኃላፊዎች የኮሮናቫይረስ ክትባት የበለጠ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ቀድሞ የሚታደልበት አማራጭ ላይ ቀድመው እንዲዘጋጁ ማሳሰቡ ተነገረ። ሲዲሲ ትናንት በድረ-ገጹ ላይ ባወጣው ጽሑፍ ላይ ክትባቱ ለበሽታው የበለጠ ተጋለጭ ለሆኑ ሰዎች እስከ ጥቅምት አጋማሽ ሊሰራጭ እንደሚችል ጠቁሟል። “ሲዲሲ ግዛቶች ቀድመው እንዲዘጋጁ በማሰብ ዝግጁ ሊሆን የሚችል የክትባት መጠን እና ጊዜን ለግዛቶች አሳውቋል። ከጥቅምት አጋማሽ እስከ ሕዳር መጨረሻ... | https://www.bbc.com/amharic/news-54012503 |
sports | ማንችስተር ሲቲ የእንግሊዝ ፕሪምየር አሸናፊ ሆነ | ማንችስተር ሲቲ በአራት ዓመታት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ የዘንድሮው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሆኗል። ትናንት ምሽት በደረጃ ሰንጠረዡ ሁለተኛ ላይ የሚገኘው ማንቸስተር ዩናይትድ በሌስተር ሲቲ መሸነፉን ተከትሎ ነው ሲቲዎች አሸናፊነታቸውን ያረጋገጡት። የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን አሸናፊነቱን ያረጋገጠው ሦስት ጨዋታዎች እየቀሩ ከማንችስር ዩናትድ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት10 በመሆኑ ነው። ማንችስተር ሲቲ የዘንድሮውን ጨምሮ በአጠቃላይ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሰባት ጊዜ አሸናፊ መሆን ችለዋል። ይህ ደግሞ በዘጠ... | https://www.bbc.com/amharic/57084282 |
health | የታንዛኒያው ፕሬዝደንት የኮቪድ-19 ክትባት ለታንዛኒያውያን አያስፈልግም አሉ | የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ የአገሪቱ ጤና ባለስልጣናት የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመጠቀም ከመወሰናቸው በፊት ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው አሉ። ማጉፉሊ ምንም አይነት ማረጋገጫ ሳያቀርቡ የኮቪድ-19 ክትባት ሕዝቡን ሊጎዳ ይችላል ብለዋል። "የጤና ሚንስቴር ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ጥናቶችን ሳያከናውኑ እነዚህን ክትባቶች ለመሞከር መፍጠን የለባቸውም። ሁሉም ክትባት ለእኛ ጠቃሚ አይደሉም፤ መጠንቀቅ አለብን። መሞከሪያ መሆን የለብንም" ሲሉ ማጉፉሊ ተናግረዋል። "ክትባቶች አደገኛ ናቸው። ነጩ ሰውዬ... | https://www.bbc.com/amharic/55825410 |
sports | ስኮትላንድ እግር ኳስ ተጫዋቾች ‘የቴስታ’ ኳሶችን እንዳይመቱ ልታግድ ነው | በስኮትላንድ ያሉ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ከጨዋታ አንድ ቀን በፊት እና በኋላ ኳስ በጭንቅላት (በቴስታ) እንዳይመቱ ሊታገዱ ነው። ክለቦችም የጭንቃላት ኳስ የሚበዛባቸው የልምምድ ቀኖችን በሳምንት ወደ አንድ እንዲቀንሱ ተጠይቀዋል። ውሳኔው የግላስጎው ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ጥናት እግር ኳስ ተጫዋቾች ከሦስት እጥፍ በላይ ከጭንቅላት ጋር በተያያዘ በሽታ እንደሚሞቱ ማሳየቱን ተከትሎ የመጣ ነው። ባለሙያዎች ችግሩ ኳስን በተደጋጋገሚ በጭንቅላት ከመምታት ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ጠቁመዋል። የስኮትላንድ እግር... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cn0jy82pyl2o |
politics | ሩሲያ በዩክሬን ላይ 'መጠነ ሰፊ ጥቃት ልትፈፅም' እንደምትችል አሜሪካ አስታወቀች | የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የሩሲያው ቭላድሚር ፑቲን ከፍተኛ ውጥረት የነገሰባት ዩክሬንን በተመለከተ በመጪው ማክሰኞ በቪዲዮ እንደሚነጋገሩ ዋይት ሃውስ አስታውቋል። ከሰሞኑ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሩሲያ በዩክሬን ላይ "መጠነ ሰፊ ጥቃት ለመፈጸም" እቅድ እንዳወጣች የሚያሳይ ማስረጃ አገራቸው እንዳገኘች ገልጸዋል። ነገር ግን ፕሬዚዳንት ፑቲን ዩክሬንን ለመውረር የመጨረሻ ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ግልጽ አይደለም ሲሉም አክለዋል። ሩሲያ በበኩሏ የማጥቃትም ሆነ የመውረር ሃሳብን... | https://www.bbc.com/amharic/news-59537669 |
health | ለህሙማን ሌላ ህመም የሆነባቸው የመንግሥት ጤና ተቋማት ዋጋ ጭማሪ | ሠላማዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ ናት። እናቷ ባለባቸው ህመም ምክንያት በየጊዜው ሐኪም ቤት ይመላለሳሉ። ሁሌም እንደምታደርገው እናቷ ላለባቸው ቀጠሮ በቅርቧ ወደሚገኘው ጤና ጣቢያ ይዛቸው ታቀናለች። ጤና ጣቢያውን ከቅርበቱም በላይ በዋጋውም ተመራጭ ነው። ስትደርስ የገጠማት ግን ከከዚህ በፊቱ የተለየ ነው። ዋጋው አይቀመስም። ካላቸው አቅም አንጻር ያልጠበቁትም ነው። "5 ብር የነበረው የካርድ ዋጋ 50 ብር ደርሷል።" "ካርድ ብቻም አይደለም። ሁሉም የአገልግሎቶች ዋጋ ጨምሯል" ትላለች ሠላማዊት። ህክምና ላይ... | https://www.bbc.com/amharic/news-58220082 |
health | ፕሬዝደንት ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ "ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው" አሉ | በአሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ ሰዎች የአፍ እና አፍንጫ ጭምብል የማድረግ ግዴታ የለባቸውም መባሉን ተከትሎ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው ብለዋል። ባለስልጣናት በአሜሪካ የኮሮናቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ከውስን ቦታዎች በስተቀር ያለጭምብል መንቀሳቀስ ይችላሉ ብለዋል። አካላዊ ርቀትን መጠበቅም አይጠበቅባቸውም ተብሏል። ከዚህ ውሳኔ በኋላ "ኦቫል" ቢሮ ከሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎች ጋር ፕሬዝዳንቱ ራሳቸው ያለጭምብል ታየተዋል። ይሁን እንጂ እንደ አወቶብስ፣... | https://www.bbc.com/amharic/57111329 |
politics | ቦክሰኛው ማኒ ፓኪዮ ለፕሬዘዳንትነት እንደሚወዳደር ይፋ አደረገ | በዓለም የቦክስ ውድድር መድረኮች ኮከብ የሆነው ፊሊፒንሳዊው ማኒ ፓኪዎ በቀጣይ ዓመት በሚደረገው ምርጫ ለፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደር ይፋ አደረገ። ፓኪዮ ገዢውን ፓርቲ በሚቀናቀነው ፒዲፒ-ላባን ፓርቲ አማካኝነት ነው ዕጩ ተወዳዳሪ ሆኖ ለምርጫው የሚቀርበው። በበርካታ ድሎች ከታጀበው ቦክሰኝነቱ ባሻገር የ42 ዓመቱ ፓኪዎ በፊሊፒንስ ፓርላማ ውስጥ ሴናተርም ነው። በስልጣን ላይ የሚገኙት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ለሌላ የስልጣን ዘመን መወዳደር ባይችሉም አንድ ተፎካካሪ ፓርቲ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ዕጩ አድርጎ አቅርቧ... | https://www.bbc.com/amharic/58621504 |
sports | ቶኪዮ ኦሊምፒክ፡ አውስትራሊያ የኦሊምፒክ ተሳታፊዎችን ለማስተዋወቅ የለቀቀችው ፎቶ አወዛገበ | የአውስትራሊያ ኦሊምፒክ ቡድን ተወዳዳሪዎችን ለማስተዋወቅ የለጠፈው ፎቶ ውግዘት ገጥሞታል። የአውስትራሊያን የኦሎምፒክ ቡድን ለማስተዋወቅ ይፋ የተደረገው ፎቶ ብዝሃነትን አያንጸባርቅም በሚል አንዲት ጥቁር ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ራሷን ከውድድሩ ልታቅብ እንድምትችል አስጠንቅቃለች። የአውስትራሊያን የኦሊምፒክና ፓራሊምፒክ [የአካል ጉዳተኞች የሚሳተፉበትን] ተሳታፊዎች ትጥቅን ለማስተዋወቅ የተለቀቀው ምስል ላይ የሚታዩ ሰዎች በሙሉ ተመሳሳይ የቆዳ ቀለም ያላቸው ናቸው። እናም በሀገሪቱ እውቅና ያላት ጥቁር የቅርጫት... | https://www.bbc.com/amharic/news-57027326 |
sports | በኳታር የዓለም ዋንጫ ተጫዋቾች እና ተመልካቾች እንዳያደርጉ የተከለከሉት ነገሮች የትኞቹ ናቸው? | እየተካሄደ ያለው የኳታር የዓለም ዋንጫ ውድድር በርካታ ድንቅ ነገሮች እየታዩበት ከመሆኑ በተጨማሪ ውዝግቦችንም እያስተናገደ ነው። ኳታር በባሕረ ሰላጤረው በረሃ ውስጥ አጀብ ያሰኙ ስታዲየሞችን ገንብታ በአረቡ ዓለም የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ በማስተናገድ ታሪክ አስመዝግባለች። በተጫማሪም ይህ የዓለም ዋንጫ ከቀደሙት በተለየ በርካታ ትችቶች የተሰነዘሩበት ነው። ኳታር ከእምነት እና ከሕጓ አንጻር የተለያዩ ክልከላዎችን የጣለች ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ ድጋፍ እና ውግዘት ከተለያዩ ወገኖች እየተሰነዘሩባት ነው። ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1kg2n80jqo |
business | ኤሚሬትስ ገንዘቤን አላገኘሁም በሚል ወደ ናይጄሪያ የሚደርገውን በረራ ሊያቋርጥ ነው | ግዙፉ የዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ አየር መንገድ ወደ ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ናይጄሪያ የማደርገውን በረራ ሊያቋርጥ መሆኑን አስታወቀ። ዋና መቀመጫውን ዱባይ ያደረገው ኤሚሬትስ አየር መንገድ የናይጄሪያ በረራውን ከነሐሴ 26/2014 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሚያቆም ገልጿል። ኤሚሬትስ ወደ ናይጄሪያ እና ከናይጄሪያ የሚያደርገውን በረራውን ለማቆም የወሰነው በአገሪቱ ያለውን ገንዘብ ማግኘት ባለመቻሉ መሆኑን አስታውቋል። ኢሚሬትስ አየር መንገድ በአገሪቱ ሲሰጥ ለቆየው የአየር ትራንስፖርት አገለግሎቱ ከናይጄሪያ ማግኘ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/c848nyg3rplo |
politics | ሊዝ ትረስ፡ ስልጣን እንዲለቁ ያስገደዷቸው 3 መሠረታዊ ጉዳዮች | ሊዝ ትረስ ወደ ዶውኒንግ ስትሪት ከመጡ በ6ኛው ሳምንታቸው ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል። ገና በ45ኛ ቀናቸው ስልጣን መልቀቃቸው በዩኬ ታሪክ ለአጭር ጊዜ ስልጣን ላይ የቆዩ ሰው ያደርጋቸዋል። ሊዝ ትረስ የወግ አጥባቂ መሪነት ቦታን ከቦሪስ ጆንሰን ተረክበው ለ6 ሳምንታት የዩኬ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነዋል። ከዚህ ቀደም ዩኬን ለአጭር ጊዜ በጠቅላይ ሚንስትርነት የመሩት ጆርጅ ካኒንግ ነበሩ። ጆርጅ ካኒንግ ሞት ሳይቀድማቸው እአአ 1872 ላይ ዩኬን ለ119 ቀናት መርተው ነበር። ጠቅላይ ሚንስትሯን ስልጣን ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cerd038x0yro |
sports | የሱዳኑ ክለብ ከጊዮርጊስ ጋር ያለው ግጥሚያ ከኢትዮጵያ ውጪ ይሁንልኝ አለ | የሱዳኑ እግር ኳስ ክለብ ከኢትዮጵያው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚያደርገው የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከኢትዮጵያ ውጪ ይሁንልኝ ሲል ካፍን ጠየቀ። አል-ሂላል ኦምዱርማን እግር ኳስ ክለብ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ሊደረግ የታሰበው ውድድር ከኢትዮጵያ ውጪ እንዲሆን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንን (ካፍ) የጠየቀው በደኅንነት ስጋት ነው። በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ዳግም ማገርሸቱ የደኅንነት ስጋት እንዳሳደረበት ክለቡ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ የገለጸ ሲሆን ካፍም ለጥያቄው ምላሽ እንደሚሰ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cw9d804p33lo |
health | ዩናይትድ ኪንግደም ጤነኛ ሰዎችን በኮቪድ ተህዋሲ 'ልትለክፋቸው' ነው | የኮቪድ ክትባትን በማግኘት ጥረት ውስጥ ከፊት ከሆኑ አገራት አንዷ የሆነችው ዩናይትድ ኪንግደም የተለየ አይነት የክትባት ሙከራ ለማድረግ ቀዳሚዋ አገር ልትሆን ነው። በጥር ወር ላይ 90 ጤነኛ ሰዎች ሆን ተብለው ለኮቪድ ተህዋሲ እንዲጋለጡ በማድረግ ነው አዲሱ ሙከራ የሚደረገው። ይህም ቶሎ ክትባት ለማግኘት ይረዳል ተብሏል። መንግሥት ከወዲሁ 33.6 ሚሊዮን ፓውንድ ለዚሁ ሙከራ መድቧል። ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግበታል የተባለው ይህ አዲስ የሙከራ ዘዴ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ከአገሪቱ መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥል... | https://www.bbc.com/amharic/54617479 |
politics | ባይደን የሚቀለብሷቸው የትራምፕ ውሳኔዎች የትኞቹ ናቸው? | አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን 50 ዓመታት በፖለቲካው ውስጥ አሳልፈዋል። በአስተዳደር ዘመናቸው ይወስዷቸዋል ተብለው ከሚጠበቁ እርምጃዎች አንዱ አሜሪካን ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት መመለስ ነው። የቀድሞው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያስተላለፏቸው አወዛጋቢ ውሳኔዎችን ባይደን ይቀለብሳሉ ተብሎም ይጠበቃል።ከነዚህ መካከል በሙስሊም አገራት ዜጎች ላይ ተጥሎ የነበረው የጉዞ እገዳ ይገኝበታል። ከባይደን አጀንዳዎች አንዱ አሜሪካን ወደ ዓለም ጤና ድርጅት አባልነቷ መመለስ ነው። ትራምፕ ድርጅ... | https://www.bbc.com/amharic/55735398 |
sports | እውቁ የቴኒስ ተጫዎች ጆኮቪች ከአውስትራሊያ ተባረረ | የዓለማችን ቁጥር አንድ የሜዳ ቴኒስ ኮኮብ ኖቫክ ጆኮቪች በአውስትራሊያ ለመቆየት ባደረገው የመጨረሻ ፍርድ ቤት ክርክር ተረትቶ አገሪቱን ለቆ እንዲወጣ ተደረገ። ክትባት ለመቀበል አሻፈረኝ ያለው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቹ፤ የአገሪቱ መንግሥት "በጤና እና ባልተገባ ስነምግባር" ምክንያት ቪዛውን መሰረዙን ተከትሎ ጆኮቪች ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ቢወስደውም ፍርድ ቤቱም ይግባኙን ውድቅ አርጎበታል። በውሳኔው "በጣም ቅር ብሎኛል" ያለው ጆኮቪች ውሳኔው ተቀበሎ ወደ ዱባይ አቅንቷል። አገሩ ሰርቢያ 'በአውስትራልያ ኦፕን... | https://www.bbc.com/amharic/60020796 |
politics | የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ከመንግሥት ባለሥልጣንና ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር ተወያዩ | የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ማይክ ሐመር አርብ አዲስ አበባ በመግባት ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና ከተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጋር ተወያዩ። በቅርቡ የተሾሙት ልዩ መልዕክተኛው ካለፈው ሳምንት ማብቂያ በጀመሩት ጉዟቸው በቀዳሚነት ወደ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና ግብፅ ከተጓዙ በኋላ ነው አዲስ አበባ ያቀኑት። ልዩ መልዕክተኛው አዲስ አበባ እንደገቡ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ከኦነግ እና ከኦፌኮ ሊቃነ መናብት ጋር ተገናኝተው ውይይት አድ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/c80dpn08pn1o |
sports | እግር ኳስና ኮሮናቫይረስ፡ የኢትዮጵያን ስም በአውሮፓ ያስጠራችው ሎዛ | ሎዛ አበራ በማልታ በሴቶች ዘርፍ የ2019/2020 የውድድር ዘመን ምርጥ ተጫዋች በመሆን በማልታ የእግርኳስ ተጫዋቾች ማህበር ተሸልማለች። ሎዛ ለቢቢሲ አዲስ አይደለችም። የማልታውን ቡድን ቢርኪርካራ እንደተቀላቀለች እንዴት ነው ሕይወት በአውሮፓ ስንል አናግረናት ነበር። ከዚያ ቃለ ምልልስ በኋላ ሎዛ ብዙ ታሪክ ፅፋለች። ሪከርድ ሰብራለች። ሎዛ ለሌሎች አንጋፋ የስፖርት መገናኛ ብዙሃንም አዲስ አይደለችም። ከጎል ዶት ኮም ጀምሮ እስከ ካፍ ኦንላይን ስለሎዛ አውርተው አይጠግቡም። ቡድኗ ቢርኪርካራ ተቃናቃኙ ሂ... | https://www.bbc.com/amharic/news-54101682 |
business | ፓኪስታን ዜጎቿ የሻይ ፍጆታቸውን እንዲቀንሱ ጠየቀች | የፓኪስታን ዜጎች በአገሪቱ ያለውን የምጣኔ ሃብት ቀውስ ለማረጋጋት የሚጠጡትን የሻይ መጠን እንዲቀንሱ ተጠየቁ። የፓኪስታን ከፍተኛ ሚኒስትር አህሳን ኢቅባል፣ በቀን ጥቂት ብርጭቆ ሻይ መጎንጨት ፓኪስታን የሻይ ቅጠል ምርትን ከውጪ ለማስገባት የምታወጣውን ወጪ ይቀንሳል ብለዋል። በአገሪቱ ያለው የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከውጭ የሚገባ ማንኛውም ምርት ለመግዛት የሚበቃው ከሁለት ወር ላነሰ ጊዜ ብቻ ነው ተብሏል። ይህም አገሪቷን አስቸኳይ የገንዘብ እርዳታ እንድትፈልግ አስገድዷታል። ፓኪስታን ባለፈው ዓመት ከ600 ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1zzww9vrpo |
politics | ንግሥቲቱ እና አፍሪካ: ረጅም ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት | የያኔዋ ልዕልት ኤልዛቤጥ በኬንያ ገጠራማ ሥፍራ በሚገኘውና በአረንጓዴ ተክሎች፣ በረጃጅም ዛፎች እና በዱር አራዊት በተከበበው ትሬቶፕስ ሆቴል ሲደርሱ አባታቸው ንጉስ ጆርጅ ስድስተኛ አረፉ።በዚያም በ25 ዓመታቸው የንግሥትነት ሥፍራውን ያዙ። ንግሥት ኤልዛቤጥ ሁለተኛ በሰባ ዓመት የንግሥና ዘመናቸው ከ20 በላይ የአፍሪካ አገሮችን ጎብኝተዋል። በአንድ ወቅት ለቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ ከማንኛውም ሰው በላይ የአፍሪካ አገራትን ጎብኝቻለሁ በማለት በዙሪያቸው ያሉ ሰዎችን ፈገግ አሰኝተው ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/c514xy2zzqqo |
health | የኮሮናቫይረስ ወረርሸኝ አዲስ አይነት የአእምሮ ጤና እክል ይዞ መጥቷል ተባለ | በኮሮናቫይረስ ከሚያዙ ሰዎች በእያንዳንዱ 17 ሰው አንድ ሰው ከባድ ጭንቀት፣ ድብርት እና እንቅልፍ ማጣት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚያጋጥመው አንድ አሜሪካ ውስጥ የተሰራ ጥናት ጠቁሟል። ይህ ቁጥር ታዲያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች የሚያጋጥማቸው እንዲህ አይነት የጤና እክል ከሌሎች በሽታዎች ጋር ሲነጻጸር እጥፍ እንደሆነ ደርሰንበታል ይላሉ ጥናቱን ያካሄዱት ባለሙያዎች። በጥናቱ መሰረት ባልተጠበቀ ሁኔታ የቀደም የአእምሮ ጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች በኮሮናቫይረስ የመያዝ እድላቸው ከጤናማ ሰዎች ጋር ሲነጻጸር 6... | https://www.bbc.com/amharic/news-54885168 |
politics | ሊዝ ትረስ ከንግሥቲቱ ጋር ከተገናኙ በኋላ በይፋ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ | ትናንት ሰኞ የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ ሆነው የተመረጡት ሊዝ ትረስ ዛሬ ማክሰኞ ከንግሥት ኤልዛቤጥ ሁለተኛ ጋር ከተገኙ በኋላ በይፋ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ። ሊዝ ትረስ ወደ ባልሞራል ቤተ-መንግሥት ተጉዘው ንግሥት ኤልዛቤጥን ያገኙት በይፋ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የተለመደ አካሄድን መከተል ስላለባቸው ነው። የዩኬ እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤጥ ዳግማዊት በ70 ዓመት የንግሥና ዘመናቸው ሊዝ ትረስ 15ኛ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው። አዲሷ ጠቅላ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cx9g7ydydlzo |
business | ዓለም ባንክ ለኮሮናቫይረስ ድንገተኛ እርዳታ 12 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገባ | የዓለም ባንክ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ትግል ውስጥ ያሉ አዳጊ አገራትን ያግዝ ዘንድ የ12 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገብቷል። ዓለም ባንክ ገንዘቡን የሚሰጠው በብድር፣ በእርዳታና በቴክኒክ ድጋፍ መልክ ሲሆን ባንኩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የዓለም መሪዎች ኮሮናቫይረስ ኢኮኖሚያቸውን እንዳያሽመደምድ ብርቱ ዝግጅት ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ነው። ኮሮናቫይረስ ኢኮኖሚዎች ላይ የሚያስከትለው መቀዛቀዝ አገራትን ችግር ውስጥ ሊከት እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል። ይህ የዓለም ባን... | https://www.bbc.com/amharic/51716797 |
sports | የስፖርት ውርርድ አዲሱ የወጣቶች ሱስ ይሆን? | ሄኖክ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚኖር ወጣት ነው። ከስድስት ወር በፊት በጓደኞቹ ገፋፊነት የጀመረው በስፖርት ውድድሮች ላይ ገንዘብ ማስያዝ መወራረድ ሱስ እየሆነበት እንደመጣ ይናገራል። ''ከገንዘብ ጋር የተያያዘ እንደመሆኑ መጠን እራስን ለመቆጣጠር ትንሽ ይከብዳል። በሳምንቱ መጨረሻ በሚደረጉ በተለይ የእንግሊዝና ሌሎች የአውሮፓ ሊጎች ላይ ሳላስይዝ አላልፍም''ይላል። • ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ በትንሹ ከ10 ብር ጀምሮ እስከ 200 ብር ድረስ በአንድ ጊዜ እንደሚያስይዝ የሚናገረው ሄኖክ ... | https://www.bbc.com/amharic/news-49835538 |
business | ኮሮናቫይረስ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ምን አሉ? | ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ትናንት አርብ አመሻሽ ላይ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን በተመለከተ በጽህፈት ቤታቸው መግለጫ ሰጥተወው ነበር። በዚህ መግለጫቸው ላይም የኢኮኖሚ፣ የጸጥታ፣ የጤና እና የማህበራዊ ጉዳዮች ኮሚቴ ተቋቁሞ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ሲከታተል መቆየቱን አስታውቀዋል። በዚህም መሠረት አዳዲስ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ተወስኗል በማለት ውሳኔዎቹን ገልፀዋል።. ማንኛውም ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ ሰው ለ14 ቀናት በራሱ ወጪ ወደ ለይቶ ማቆያ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ አየር መ... | https://www.bbc.com/amharic/51986050 |
health | ኮሮናቫይረስ፡ የአሜሪካውያን የኮቪድ-19 ክትባት ምርጫ ለምን የተለያየ ሆነ? | አሜሪካ ሦስት ክትባቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ የፈቀደች ሲሆን ሰዎች የሚፈልጉትን እየመረጡ ነው። ሦስቱም የኮቪድ-19 ክትባቶች በቫይረሱ መያዝና ተይዞ ሆስፒታል መግባትን እንዲሁም ሞትን በመከላከል ረገድ ውጤታማ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ የጤና ባለሥልጣናት ለዜጎች የሚሰጠው የተሻለው ክትባት ነው ብለዋል። ቢሆንም ከጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ይልቅ ፋይዘር እና ሞደርና ክትባቶችን የሚመርጡ ብዙዎች ናቸው። በመጋቢት መጀመሪያ የዲትሮይት ከንቲባ ማይክ ዱጋን የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባትን ውድቅ አድርገው በአሜሪ... | https://www.bbc.com/amharic/news-56498267 |
business | ዩናይትድ ኪንግደም ለታዳጊ አገራት ምርቶች የቀረጥ ቅነሳ ልታደርግ ነው | ዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ግንኙነቷን ለማሳደግ ከታዳጊ አገራት ከምታስገባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ምርቶች ላይ ቀረጥ ልትቀንስ ነው። ይህ ለታዳጊ አገራት የታሰበው የንግድ ዕቅድ በጥር ወር ተግባራዊ ይሆናል። ይህም ዩናይትድ ኪንግደም የአውሮፓ ኅብረት አባል በነበረችበት ጊዜ በነበረው ዕቅድ ላይ ይመሠረታል ተብሏል። በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በስፋት የማይመረቱ እንደ ልብስ፣ ጫማ እና ምግቦች ያሉ ዕቃዎች ዝቅተኛ ወይም ዜሮ ታሪፍ ይጣልባቸዋል። ዕቅዱ 65 ታዳጊ አገራትን ያጠቃልላል ተብሏል። ዕቅዱ በማደግ ላ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/crg7pp8x210o |
politics | የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለአዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስልጣን አስረከበ | የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት አዲስ ለተመሰረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዛሬው ዕለት ስልጣን አስረክቧል። ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 24፣ 2014 ዓ.ም በስድስተኛው ዙር 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነው የስልጣን ርክክቡን አዲስ ከተቋቋመው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጋር ያደረገው። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢትዮጵያ 11ኛው ክልል በመሆን በፌዴሬሽን ምክር ቤት እውቅናን ያገኘው በባለፈው ሳምንት መስከረም 20፣ 2014 ዓ.ም ነው። 11ኛው... | https://www.bbc.com/amharic/news-59151038 |
business | መዳብ ተብሎ ድንጋይ የተሸጠለት ድርጅት 36 ሚሊዮን ዶላር ተጭበረበረ | ባለፈው የፈረንጆች ዓመት 36 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት መዳብ ከቱርክ ኩባንያ የገዛው ድርጅት ቀለም የተቀባ ድንጋይ እንደደረሰው አስታወቀ። አንድ የሸቀጣ ሸቀጥ ነጋዴ በ36 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት የገዛውን መዳብ፤ አቅራቢ ኩባንያው ቀለም በተቀቡ ድንጋዮች ቀይሮ እንዳስረከበው ገልጿል። መቀመጫውን ጄኔቫ ያደረገው ሜርኩሪያ ኢነርጂ ግሩፕ 10,000 ቶን የመዳብ ግዢ መፈጸሙን ተከትሎ በጭነት ማጓጓዝ (ካርጎ) ወቅት ተጭበርብሬያለሁ ብሏል። ጭነቶቹ ቻይና ሲደርሱ በመዳቡ ምትክ ቀለም በተቀቡ ድንጋዮች የተሞሉ ኮን... | https://www.bbc.com/amharic/news-56343133 |
politics | ምርጫ ቦርድ ‘ኢሠፓ’ በሚል ስም የቀረበውን የፓርቲ ምዝገባ ጥያቄ ውድቅ አደረገ | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “የኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ፓርቲ (ኢሠፓ)” በሚል ስያሜ የቀረበውን የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ምዝገባ ጥያቄን ውድቅ አደረገ። ከ30 ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ብቸኛው ገዢ ፓርቲ የነበረው ኢሠፓ፣ ሕገወጥ ተብሎ ከአገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ከተገለለ በኋላ በስሙ ለመደራጀት ጥያቄ የቀረበው ባለፈው ግንቦት ወር ነበር። ቦርዱ የኢ.ሕ.ድ.ሪ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም ከመሠረቱ ፓርቲ ጋር በተመሳሳይ ስም ለመመዝገብ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ያደረገባቸውን ሕጋዊ ምክንያቶች ዘር... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cg656qpdgypo |
politics | የአርጀንቲና ምክትል ፕሬዝዳንት ከግድያ ሙከራ ለጥቂት አመለጡ | የአርጀንቲና ምክትል ፕሬዝዳንት ክርስቲና ፈርናንዴዝ ዴ ኪርችነር ትላንት ሃሙስ ምሽት ከግድያ ሙከራ ለጥቂት አመለጡ። ምክትል ፕሬዝዳንቷ በጥይት ከመመታት የዳኑት የተኳሹ መሳሪያ በመንከሱ ነው ተብሏል። ዴ ኪርችነር ከመኖሪያ ቤታቸው ውጪ ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው ሰላምታ በመስጠት ላይ ሳሉ ነበር አንድ ግለሰብ ከሕዝቡ መካከል ወጥቶ ፊታቸው ላይ ሽጉጡን አነጣጥሮ ለመተኮስ የሞከረው። የአርጀንቲና ፕሬዝዳንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ ምክትል ፕሬዝዳንቷ ፊት ላይ ተነጣጥሮ የነበረው ጦር መሳሪያ አምስት ጥይቶች ጎርሶ ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1lk573xk7o |
business | ክሪፕቶከረንሲዎች ለከፍተኛ ኪሳራ እንደተጋለጡ የግብይት ባለሙያዎች አስጠነቀቁ | ክሪፕቶከረንሲን ጨምሮ ሌሎችም የበይነ መረብ ገንዘብ ማዘዋወሪያዎች አደጋ እንዳንዣበበባቸው የሆንግ ኮንግን የግብይት ተንታኞች ማስጠንቀቂያ ሰጡ። “ኢንቨስተሮች ከፍተኛ አደጋ ማንዣበቡን ይገንዘቡ” ሲል 'ሴኪውሪቲስ ኤንድ ፊውቸርስ' ኮሚሽን የተባለው የባለሙያዎች ማኅበር አሳውቋል። ማስጠንቀቂያውን የተሰጠው የክሪፕቶከረንሲ ገበያ በውዝግብ በተሞላበት ጊዜ ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኤፍቲኤክስ ክሪፕቶከረንሲ መሥራች ሳም ባንክማን-ፍሬድ በዚህ ሳምንት ታስሮ ክስ ተመሥርቶበታል። “አንዳንድ የበይነ መረብ ሀብት ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/c72nyeppxm0o |
health | ኮሮናቫይረስ፡ ደቡብ ኮርያ የኮቪድ-19 ስርጭት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ሕጓን አጠበቀች | በደቡብ ኮርያ ዋና ከተማ የኮቪድ-19 ስርጭት መስፋፋቱን ተከትሎ ሙዚየሞች፣ የምሽት ጭፈራ ቤቶች፣ እንዲሁም መጠጥ ቤቶች ተዘግተዋል። ማክሰኞ ዕለት የቫይረሱ ስርጭት ለአምስተኛ ቀን ወደ ሶስት ዲጂት ከፍ ያለ ሲሆን በአብዛኛው እድሜያቸው በ40ዎቹ ውስጥ የሆኑ ሰዎች መጠቃታቸው ታውቋል። ደቡብ ኮርያ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን በፍጥነት በመቆጣጠር ስሟ በተደጋጋሚ ሲነሳ ነበር። ነገር ግን ከቤተ እምነቶች ጋር በተያያዘ የተቀሰቀሰው ዳግም ወረርሽኝ ስጋትን አጭሯል። ደቡብ ኮርያ ማክሰኞ ዕለት 246 ሰዎች በቫይረሱ... | https://www.bbc.com/amharic/news-53831241 |
health | ኮሮናቫይረስ፡ 33 ሚሊዮን ፓውንድ ያሰባሰቡት የ100 አመቱ ሽማግሌ በኮቪድ-19 ሞቱ | በእንግሊዝ ለጤና ባለሙያዎች ያላቸውን ክብር ለመቸር 33 ሚሊዮን ፓውንድ በማሰባሰብ ከፍተኛ ስም ያተረፉት ካፕቴን ቶም ሙር በመቶ አመታቸው በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው አልፏል። 33 ሚሊዮን ፓውንድ ለአገሪቱ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት ወይም ኤንኤችኤስ ማሰባሰብ የቻሉት የ100 አመቱ የዕድሜ ባለፀጋ በባለፈው ሳምንት መጨረሻ እሁድ ከመተንፈሻ እክል ጋር በተያያዘ ቤድፎርድ ወደተባለ ሆስፒታል ተወስደው ነበር። ልጃቸው፣ ሃና ኢንግራም ሙር በባለፉት ሳምንታት በሳንባ ምች ህመም ሲሰቃዩ እንደነበርና በዚህ ሳምንት በኮ... | https://www.bbc.com/amharic/news-55909539 |
health | ኖርዌይ ፡ በአንድ ዋሻ ውስጥ ሲዝናኑ የነበሩ ሰዎች በጭስ ታፍነው ሆስፒታል ገቡ | በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ውስጥ በሚገኝ በአንድ ከመሬት በታች ባለ ዋሻ ውስጥ ተሰባስበው እየተዝናኑ ከነበሩ ሰዎች መካከል ከ20 የሚበልጡት በካርበን ሞኖክሳይድ ጭስ ታፍነው በመመረዛቸው ሆስፒታል መግባታቸው ተነገረ። ግለሰቦቹ ሊገኙ የቻሉት በአካባቢው ቅኝት ሲያደርጉ የነበሩ ፖሊሶች በዋሻው ውስጥ ከነበሩት መካከል የተወሰኑት ራሳቸውን ስተው ወደ ጎዳና በመውጣት ወዲያ ወዲህ ሲሉ ካገኟቸው በኋላ ነው። ከዚህም በኋላ ሌሎቹ ጓደኞቻቸው በጭሱ ታፍነው ከዋሻው ውስጥ በመውጣታቸው አምቡላንስ ተጠርቶ ወደ ሆስፒታል... | https://www.bbc.com/amharic/news-53967065 |
business | ከ20 ሺህ ብር በላይ የሚወጣበት የኢትዮጵያ ዘመናዊ የንቅሳት ገበያ | ሰውነታቸው ላይ ንቅሳት ለማሳረፍ ወደ ንቅሳት ቤቶች ጎራ ከሚሉ ሰዎች መካከል በፍቅር ወይም በትዳር የተጣመሩ ጥንዶች ይገኙበታል። "ጥንዶቹ ፍቅራቸውን ለመግለጽ ሴቷ የወንዱን፣ ወንዱ ደግሞ የሴቷን ስም አሊያም የስም መጀመሪያ ፊደላትን መነቀስ የተለመደ ሆኗል" ይላል የንቅሳት ባለሙያው (ታቱ አርቲስት) ሔኖክ ጥላሁን። ሆኖም በጥንዶቹ መካከል ንፋስ ገብቶ መራራቅ ሲመጣ "ለየብቻ ይመጡና ንቅሳቱን ቀይርልኝ" ብለው እንደሚጠይቁት ይናገራል። ይህንን በመሰሉ አጋጣሚዎች የተሞላውን የንቅሳት ሥራ፤ ሰዎች ሐሳባቸው... | https://www.bbc.com/amharic/news-57390536 |
business | በቱኒዝያ በሺዎች የሚቆጠሩ የተፎካካሪ የፓርቲ አባላት ፕሬዚዳንት ሳዒድን ለመቃወም አደባባይ ወጡ | በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በቱኒዚያ ዋና ከተማ ጎዳናዎች ላይ የሃገሪቱን ፕሬዚዳንት ለመቃወም አደባባይ ወጥተዋል። እርስ በእርስ ጭምር የሚቃረኑ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት የተቃውሞ ሰልፎቹን በመዲናዋ ቱኒዝ አካሂደዋል። የተቀናቃኝ ፓርቲዎቹ ከ2011 ህዝባዊ አመጽ በኋላ የተገኘውን ዲሞክራሲያዊ ጉዞ እየቀለበሱ ነው ያሏቸውን ካይስ ሰኢድን "አምባገነን" ሲሉ አውግዘዋል። የምግብ እና የነዳጅ እጥረት ለፈጠረው የሃገሪቱ የኢኮኖሚ ቀውስም ተጠያቂነት አለባቸው ብለዋል። የፕሬዝዳንት ሰኢድ ተቺዎች መፈንቅለ መንግሥ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1jj288gqvo |
health | ኮሮናቫይረስ፡ ስለ አዲሱ የኮቪድ ዝርያ እስከ አሁን የምናውቃቸው 10 ነጥቦች | ኮቪድ-19 ክትባት ተገኘለት እፎይ መባል በጀመረ ገና በሳምንቱ ከወደ ብሪታኒያ መጥፎ ዜና ተሰምቷል፡፡ የኮቪድ ተህዋሲ አዲስ ዝርያ ያለባቸው ሰዎች መገኘት ነው ዜናው፡፡ በፈረንጆች ገና ይህ ያልተጠበቀ ዜና መሰማቱ ለጊዜው አውሮጳን እያመሳት ነው፡፡ ከብሪታኒያ የሚመጡ አውሮፕላኖች ላይ እግድ እያወጡ ያሉት የአውሮጳ አገራት ድንበራቸውን ጠርቅመው እየዘጉት ነው፡፡ 1ኛ፡- በብሪታኒያ በተለይም በሎንደንና አካባቢው እስከዛሬ ታይቶ የማይታወቅ የተህዋሲው ናሙና ተገኝቷል፡፡ መገኘቱ ብቻ ሳይሆን በታመሙ ሰዎች ላይ... | https://www.bbc.com/amharic/55391884 |
sports | ከእነዚህ 7 ‘ውድ’ ተጨዋቾች ዝውውራቸውን የሚያጠናቅቁ ይኖሩ ይሆን? | የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ ሌሎች የአውሮፓ ዝነኛ ሊጎች የወድድር ዘመናቸውን መጀመራቸውን ተከትሎ ክለቦች በየትኛው የሜዳ ክፍል ራሳቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው እየለዩ ነው። ቢቢሲ ስፖርት ወደ ሌሎች ክለቦች ሊዘዋወሩ የሚችሉ “ውድ” ያላቸውን 7 ተጫዋቾችና ያሏቸውን አማራጮች ተመልክቷል። ሮናልዶ ክለቡን መልቀቅ መፈለጉ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ተጫዋቹ ከአንዴም ሁለቴ ልቀቁኝ ሲል ተናግሯል። ሮናልዶ ክለቡን የሚለቀው በቻምፒየንስ ሊግ መጫወት ስለምፈልግ ነው ይበል እንጂ በቻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ የሆነ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/c51vzkg0ng0o |
sports | ለወራት በሩሲያ ቁጥጥር ስር የምትገኘው አሜሪካዊቷ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች በምን ሁኔታ ነው ያለችው? | በሚቀጥለው ወር አሜሪካ የሴቶች የቅርጫት ኳስ ውድድር ሲጀመር በሊጉ ውስጥ ደምቀው መውጣት ከቻሉት ኮከቦች መካከል አንደኛዋ አትኖርም። የፊኒክስ ሜርኩሪ ተጨዋቿ ብሪትኒ ግራይነር ካሳለፍነው የካቲት ወር ጀምሮ ሩሲያ ውስጥ ተይዛ የምትገኝ ሲሆን ዋይት ሀውስ እስካሁን በጉዳዩ ላይ ምንም መረጃ መስጠት አልቻለም። የ31 ዓመቷ ብሪትኒ ገሪነር ሩሲያ ውስጥ ከአደንዛዥ እጽ ጋር በተያያዘ እስር ቤት እንደምትገኝ ይታመናል። ሩሲያ በምትገባበት ወቅት የአየር ማረፊያው ሰራተኞችች ባደረጉባት ምርመራ በቦርሳዋ ውስጥ የእ... | https://www.bbc.com/amharic/news-61058593 |
sports | የሴቶች ዓለም ዋንጫ፡ ሴት እግር ኳሰኞች ስንት ይከፈላቸዋል? ዓለም ዋንጫ ላይ የሚሳተፉ ሃገራትስ? | የሴቶች እግር ኳስ ከጊዜ ጊዜ እያደገ የመጣ ይመስላል፤ ትኩረት መሳብም ጀምሯል። የዘንድሮውን የዓለም የሴቶች ዓለም ዋንጫ ጨዋታ 1 ቢሊዮን ተመልካቾች ይታደሙታል የሚል ግምት አለ። የሉሲዎቹ አምበል የሆነችው ሎዛ አበራ ከወንዶች ጋር ሲነፃፀር የሴቶች ክፍያ እዚህ ግባ የማይባል ነው ትላለች። በዓለም አቀፍ ደረጃስ? የባለፈው ዓለም ዋንጫ አሸናፊ የአሜሪካ አጥዊ የሆነችው ሆፕ ሶሎ የሴቶች እና የወንዶች ክፍያ ልዩነት ፊፋ ውስጥ ያለውን 'የወንድ የበላይነት' ያሳያል ስትል ትወቅሳለች። እስቲ ክፍያውን በቁጥር... | https://www.bbc.com/amharic/48591305 |
health | የኮሮናቫይረስ በአንዳንድ ምግቦች ላይ ለቀናት እንደሚቆይ ጥናት አረጋገጠ | የኮሮናቫይረስ በተለይም ታሽገው በሚሸጡ ምግቦች ላይ እንደሚቆይ የዩናትድ ኪንግደም ተመራማሪዎች ገለጹ። የአገሪቱ የምግብ ጥራት ኤጀንሲ ባሰራው ጥናት ሳይንቲስቶች ቫይረሱን ሆነ ብለው በተወሰኑ የምግብ ማሸጊያዎች ላይ በማድረግ ሙከራውን አድረገዋል። ይህም በአትክልት እና ፍራፍሬ፣ ኬክ እና ዳቦ እንዲሁም የታሸጉ መጠጦች ሙከራው ተደርጎባቸዋል። ሳይንቲስቶቹ ሳይታጠቡ ወይም ሳይበስሉ ሊበሉ የሚችሉ ምግቦችን በመምረጥ ነው ጥናቱን ያካሄዱት። ነገር ግን ይህ ሸማቾች ላይ የሚያመጣው አደጋ ያነሰ መሆኑን ገልጸዋል።... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cn0j54rpdryo |
health | ኮሮናቫይረስ፡ ኒውዚላንድ 14 በከሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች አገኘች | የኒውዚላንዷ ትልቋ ከተማ ኦክላንድ በድጋሚ የእንቅስቃሴ ገደብ ከተጣለባት በኋላ አዲስ 14 በኮሮረናቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ተገለጸ። በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ አካባቢ አራት አንድ የቤተሰብ አባላት የሆኑ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲሰማ መላው ኒውዚላንድ በድንጋጤ ተውጦ የነበረ ሲሆን የአሁኑ ደግሞ ነገሮችን አባብሷል። ከውጭ አገራት በቫይረሱ ተይዘው ከሚመጡ ሰዎች ውጪ እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ አገሪቱ ላለፉት ሶስት ወራት ምንም በቫይረሱ የተያዘ ሰው አላገኘችም ነበር። ዛሬ ከተገኙት ተጨማሪ... | https://www.bbc.com/amharic/news-53761579 |
health | “እስክሞት ልታገል”፡ የኩላሊት ህሙማን መርጃ ያቋቋመው የኩላሊት ታማሚ | የህክምና ምርመራ ውጤት! ሕይወታችንን ባላሰብነው፣ ባልጠበቅነው መንገድ ይገለባብጣል። ለኢዮብ ተወልደመድኅን ያ ክፉ ጊዜ ጥቅምት 2006 ዓ.ም ነበር። የኩላሊት ታማሚ እንደሆነ ሐኪሞች ሲገሩት። የሁለት ሴት ልጆች አባት የሆነው ኢዮብ ይህን ዜና ሲሰማ የሚገባበት ጠፋው። ባለቤቱ በድንጋጤ ከፍተኛ ሐዘን ተጫናት። አዲስ አበባ ውስጥ የተክለሐይማኖት ሰፈር ልጅ ነው። ከ1979 ዓ. ም. ጀምሮ ግን ለአምስት ዓመታት አሰበ ተፈሪ ኖሯል። ዘጠነኛ ክፍልን አብዮት ቅርስ ትምህርት ቤት ተምሮ 10ኛ ክፍል ጥቁር አንበሳ... | https://www.bbc.com/amharic/news-58126744 |
sports | የሞ ፋራህ የቀድሞ አሠልጣኝ ለአራት ዓመት ከአትሌቲክስ ታገዱ | የሞ ፋራህ ቀድሞ አሠልጣኝ፣ አልቤርቶ ሳላዛር፣ ከአበረታች መድሀኒት ጋር በተያያዘ ከስፖርት ለአራት ዓመት ታገዱ። የ61 ዓመቱ ሳላዛር የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮን የሆነው ፋራህን ማፍራት የቻለው የናይክ ኦሪጎን ፕሮጀክት ከ2011 እስከ 2017 ድረስ ሲመሩ ቆይተዋል። ውሳኔው የተላለፈው በአሜሪካው የፀረ አበረታች መድሃኒት ኤጀንሲ ለአራት ዓመት ያህል ምርመራ ሲደረግ ከቆየና ለሁለት ዓመት ያህል በፍርድ ቤት ክርክር ከተካሄደ በኋላ ነው። ምርመራው የተጀመረው ቢቢሲ በ2015 ፓናሮማ የተሰኘ ፕሮግራሙ ላ... | https://www.bbc.com/amharic/news-49889111 |
sports | የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ታዳጊዎች ኳስ በቴስታ እንዳይመቱ ሊያግድ ነው | የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ከአንጎል ጤንነት ጋር በተያያዘ የወጣ ሪፖርትን ተከትሎ ከ12 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ኳስ በቴስታ እንዳይመቱ እገዳ ለመጣል እያሰበ መሆኑ ተነገረ። በግላስጎው ዩኒቨርስቲ የሚገኙ ባለሙያዎች እንደደረሱበት የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾች አንጎልን እያዳከመ ለሞት በሚያበቃ የአንጎል በሽታ የመጋለጥ እድላቸው ከሦስት ጊዜ በላይ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። የስኮትላንድ እግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪ ከህክምና ባለሙያዎች ጋር ከተነጋገረ በኋላ ያሉ አማራጮች ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ ተ... | https://www.bbc.com/amharic/news-50198595 |
business | ኢትዮጵያ ከግዙፉ የወደብ አስተዳዳሪ ድርጅት ጋር ውል ገባች | ኢትዮጵያ ከዓለማችን ግዙፍ የወደብ አንቀሳቃሾች መካከል አንዱ ከሆነው ዲፒ ዎርልድ ጋር የስምምነት ውል ገብታለች። ስምምነቱ ኢትዮጵያን ከሶማሊንዱ በርበራ ወደብ ጋር ለማገናኘት የሚያስችል ነው ተብሏል። የዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስ ንብረት የሆነው ዲፒ ዎርልድ ፕሮጀክቱ "ቀጣናውን ለማበልፀግና ምጣኔ ሃብታዊ አቅምን ለማሳደግ ውይይት እንዲደረግ መንገድ ይከፋታል" ብሏል። ፕሮጀክቱ ከራስ ገዟ የሶማሊላንድ በርበራ ወደብ ሁለቱን ሃገራት እስከሚያገናኘው የዋጃሌ ከተማ ድረስ ይዘረጋል። የወደቡን ፕሮጀክት በትብብር ... | https://www.bbc.com/amharic/news-57029652 |
health | ኮሮናቫይረስ፡ የዓለም ጤና ድርጅት ለአዲሶቹ የኮቪድ ዝርያዎች የግሪክ ስያሜዎችን ሰጠ | የዓለም ጤና ድርጅት ለአዳዲሶቹ የኮቪድ-19 ዝርያዎች ስም ለመስጠት የሚያስችል ስርአት ማዘጋጀቱን አስታወቀ። ከዚህ በኋላም ድርጅቱ የቫይረሱን አይነቶች ለመለየት የግሪክ ፊደላትን የሚጠቀም ሲሆን በዩናይትድ ኪንግደም፣ ደቡብ አፍሪካና ሕንድ ውስጥ የታዩት አዳዲስ ዝርያዎች መጀመሪያ ስያሜ ይሰጣቸዋል። ለምሳሌም በዩናይትድ ኪንግደም የታየው አዲሱ ቫይረስ ዝርያ 'አልፋ' የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። የደቡቡ አፍሪካው 'ቤታ' የተባለ ሲሆን በሕንድ በርካቶችን ያጠቃው የቫይረስ አይነት ደግሞ 'ዴልታ' ተብሎ እንደሚጠ... | https://www.bbc.com/amharic/news-57313043 |
politics | ምርጫን ተከትሎ የተቀሰቀሰው የሶማሊያ ውዝግብ ወደ እርስ በእርስ ግጭት ያመራ ይሆን? | በሶማሊያ ሊካሄድ የታቀደው ምርጫ መዘግየቱ አለመግባባትን እና በፖለቲከኞች መካከል አለመተማመንን አባብሷል። ይህንንም ተከትሎ በመዲናዋ ሞቃዲሾ የሰዎች ሕይወት የጠፋበት አመጽ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አገሪቱን ወደ ከፋ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። በመዲናዋ ሞቃዲሾ በፌዴራል ኃይሎች እና በታጠቁ የተቃዋሚ ታማኝ ኃይሎች መካከል ከቀናት በፊት በተነሳ ግጭት ቢያንስ አስር ሰዎች ተገድለዋል። ግጭቱ ይቀጥላል በሚል በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች 'ሠላማዊ' ወደሚሏቸው መንደሮች ተሰደዋል። ክፍተቱ ለአ... | https://www.bbc.com/amharic/56916800 |
health | በኢትዮጵያ የተካሄደው እና አስር ባለሙያዎች የተሳተፉበት ተደራራቢ የልብ ቀዶ ሕክምና | የልብ ቀዶ ህክምና ከፍ ያለ ጥንቃቄን የሚጠይቅ ህክምና ሲሆን በተለይ ተደራራቢ ችግር ሲኖር ደግሞ ሥራው በእጅጉ የተወሳሰበ ስለሚሆን ከፍ ያለ ልምድና ቴክኖሎጂ ባላቸው አገራት ውስጥ እንዲካሄድ ይመከራል። ሰኞ እሁድ 18/2013 ዓ.ም ከዚህ በፊት 'ኢትዮጵያ ውስጥ አልተደረገም' የተባለ እና ስድስት ሰዓታትን የፈጀ የልብ ቀዶ ጥገና በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል። አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ኤሎዚየር የልብ ህክምና ማዕከል ውስጥ በአንድ ጊዜ ሁለት የቀዶ ህክምናው የተደረገላቸው ግለሰብ የ55 ዓመት ጎልማሳ ናቸ... | https://www.bbc.com/amharic/news-58024877 |
politics | የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር አደገኛ ዕፅ አልተጠቀምኩም አሉ | ከዓለማችን ወጣት የአገር መሪዎች አንዷ የሆኑት የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የአደገኛ ዕፅ ምርመራ ማድረጋቸውን ይፋ አደረጉ። የ36 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን ምርመራውን እንዲያደርጉ የተገደዱት በዚህ ሳምንት መባቻ በመሸታ ቤት መስመር ባለፈ ሁኔታ ሲጨፍሩ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል መውጣቱን ተከትሎ ነው። ትናንት ዐርብ አዲስ በወጣ ሌላ ተንቀሳቃሽ ምሥል ደግሞ፣ ሳና ማሪን ከአንድ የፊንላንድ ዕውቅ የሙዚቃ አቀንቃኝ ጋር ተጠጋግተው ሲደንሱ ይታያል። እነዚህ ተንቀሳቃሽ ምሥሎች ለሕዝብ ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/c9eydv2mdn1o |
health | በህንድ የተከሰተው የጥቁር ፈንገስ በሽታ በወረርሺኝነት እንዲታወጅ ጥሪ ቀረበ | በህንድ የሚገኙ ክልሎች ‹‹የጥቁር ፈንገስ›› አማካኝነት የሚከሰተው በሽታ በከፍተኛ ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ በወረርሺኝነት እንዲታወጅ የአገሪቱ የጤና ሃላፊዎች ጠየቁ። ከዚህ ቀደም እንብዛም የማይታየው እና በዚህ ፈንገስ አማካኝነት የሚከሰተው የሚውኮርማይኮሲስ በሽታ እስከ 50 በመቶ ድረስ ገዳይ ሲሆን የሚተርፉ ሰዎችም አይናቸውን ወይም የመንጋጋ አጥንት ያጣሉ። ከቅርብ ወራት ጀምሮ ግን በሺዎች የሚቆጠሩ ከ ኮቪድ ያገገሙ እና በማገገም ላይ ያሉ ሰዎች በሚውኮርማይኮሲስ ተይዘው ተገኝተዋል። የኮቪድ ህመምተኞ... | https://www.bbc.com/amharic/news-57197231 |
business | ልደት ፤ ወጣቱ ለልደቱ የተሰጠውን ውስኪ በመሸጥ የ40ሺህ ፖውንድ ቤት ሊገዛ ነው | ማቲው ሮብሰን ይባላል፡፡ አባቱ አንድ ነገር አስለምደውታል፡፡ በየዓመቱ ልደቱ ሲሆን 18 ዓመት ዕድሜ ያለው ውስኪ ገዝተው ይሰጡታል፡፡ ልጁ ውስኪውን ያጠራቅማል፡፡ አሁን 28 ዓመት ደርሷል፡፡ ሮብሰን የተወለደው እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1992 ነው። በእነዚህ ሁሉ ዓመታት አባቱ በድምሩ 5ሺህ ፓውንድ አውጥተዋል፡፡ በየዓመቱ አንድ ውስኪ ለልደቱ ለመግዛት፡፡ እስከዛሬ 28 የውስኪ ጠርሙሶችን ገዝተውለታል፡፡ የውስኪው ዓይነት ማካላን የሚባል ነው፡፡ አሁን ዋጋው ንሯል፡፡ አባትየው ለ28 ጠርሙስ ውስኪ በ28... | https://www.bbc.com/amharic/news-54053425 |
health | በኔዘርላንድስ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመቀነስ ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ ተጣለ | የኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት በአገራቸው የክረምት መግባትን ተከትሎ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ ለሦስት ሳምንታት የመገበያያ ስፍራዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና ምግብ አቅራቢዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ እገዳ መጣሉን ገለጹ። ይህም በምዕራብ አውሮፓ የመጀመሪያዋ ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ የጣለች አገር አድርጓታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጨናቂ እና ከባድ ውሳኔ ነው ያሉት እገዳ፤ መነሻው በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እና ወደ ጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ ነው ብለዋል።... | https://www.bbc.com/amharic/news-59272479 |
sports | በግማሽ ጨዋታ ጡት ማጥባት፡ የሴት ስፖርተኞች ታሪክ | "የተወሰኑ የቡድናችን አባል ነበሩ፤ ግማሽ ጨዋታ ሲሆን ወይ ጡት ለማጥባት ወይም ጡታቸውን ለማለብ ይሄዳሉ። ከዚያም ወደሜዳ ይመለሳሉ" ትላለች አንጎላዊ-አሜሪካዊቷ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኢታሊ ሉቃስ። "ይህንን ቀርቦ ማየትም ሆነ በዚህ ማለፍ የሚያስደምም ነው፤ ለየት ያለ ጥንካሬ ያስፈልጋል" በማለት ታስረዳለች። እናት መሆንና ታዋቂ ለሆነ የቅርጫት ኳስ ቡድን መጫወት እንዲሁም ለሁለቱም የሚሆን ጊዜ ማግኘት ቀላል አይደለም። እናትነትና ስፖርተኝነትን አመጣጥኖ መሄድም ፈታኝ ነው። በተለይም ሴት ስፖርተኞች በ... | https://www.bbc.com/amharic/sport-52284120 |
politics | ጆ ባይደንና ፑቲን በነገር እየተቆራቆሱ ነው | ጆ ባይደን የሩሲያውን ኃያል ቭላድሚር ፑቲንን ‹ነፍሰ በላ› ብለው ከጠሩ በኋላ በሁለቱ መሪዎች መሀል አንድ ሁለት መባባሉ አይሏል፡፡ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለተሰበቀባቸው የቃላት ጦር ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ‹ሌባን ሌባ ቢሰርቀው ምን ሊደንቀው› ዓይነት ይዘት ያለው ምላሽ በመስጠት የጀመሩት ቭላድሚር ፑቲን ጆ ባይደን ፍቃዳቸው ከሆነ በቲቪ በቀጥታ ስርጭት ይግጠሙኝ ብለዋል፡፡ ቭላድሚር ፑቲን በቴሌቪዥን በሰጡት በዚህ ቃለ ምልልስ ባላንጣቸውን አሌክሴ ናቫልኒን በመርዝ ለመግደል እንዳልሞከሩ አስተባብ... | https://www.bbc.com/amharic/news-56441604 |
sports | ሜሲ ለስድስተኛ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ሆነ | የባርሴሎና እና የአርጀንቲናው የፊት መስመር ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ የዓለማችን ምርጥ ተጫዋች በመባል ለስድሰተኛ ጊዜ የባሎንዶር ሽልማት አሸናፊ ሆነ። የ32 ዓመቱ ሜሲ ባሎንዶርን ሲያሸንፍ እ.አ.አ. ከ 2015 በኋላ የመጀመሪያው ሲሆን ለክለቡና ለአገሩ 54 ግቦችን በማስቆጠር ባለፈው ዓመት ደግሞ ከባርሴሎና ጋር የላሊጋው አሸናፊ መሆን ችሏል። • ማንችስተር ዐይኑን የጣለባቸው የአቶ ምሥጢረ ኃይለሥላሴ ልጆች • ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ሊተኳቸው የሚችሉ 7 አሰልጣኞች የሊቨርፑሉ ተከላካይ ቨርጂል ቫን ዳይክ ደ... | https://www.bbc.com/amharic/news-50640646 |
health | ኮሮናቫይረስ ፡ የአውሮፓ ሕብረት የክትባት አቅርቦት ውዝግብ ቀጥሏል | ሁለተኛው የኮሮናቫይረስ ክትባት አምራች አቅርቦትን አስመልክቶ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ የአውሮፓ ሕብረት የክትባት ስርጭትን ተስፋ አስቆራጭ አድርጎታል ተባለ፡፡ የዩናይትድ ኪንግደም መድኃኒት አምራች የሆነው አስትራዜኔካ የምርት ችግር መኖሩን መጥቀሱ አቅርቦቱ ከሚጠበቀው በታች ይሆናል ማለት ነው፡፡ የአውሮፓ ኮሚሽን በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እየሞከርኩ ነው ብሏል፡፡ በአንዳንድ የአውሮፓ ክፍሎች የፋይዘር-ባዮኤንቴክ ክትባት አቅርቦት በመቀነሱ ምክንያት ክትባቱ በመቆም ላይ ነው፡፡ ከኦክስፎርድ ዩ... | https://www.bbc.com/amharic/55777884 |
politics | የኬንያ ፕሬዚዳንት የምርጫ አስፈጻሚዎችን አገዱ | የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ነሐሴ የተካሄደውን ምርጫና አሸናፊ ያደረጋቸውን ውጤት ያልተቀበሉ አራት የምርጫ ኮሚሽነሮችን ከስራ አገዱ። ፕሬዚዳንት ሩቶ ዛሬ አርብ እንዳስታወቁት ፍርድ ቤት አራቱን ባለስልጣናት ህግ በመጣስ፣ በከባድ ስነ ምግባር ጉድለትና በብቃት ማነስ እንደሚመረምራቸውና ከስልጣናቸውም እንደሚባረሩ ገልጸዋል። ነገር ግን የተቃዋሚ ፓርቲው አመራርና ለአምስት ጊዜ በምርጫ የተወዳደሩት ራይላ ኦዲንጋ ውሳኔውን አውግዘው በመጪው 2027 ምርጫንም መንግሥት ለማጭበርበር ያለመ ነው ብለዋል። “አራ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/crgj5g616y5o |
politics | የኢትዮጵያ ኤምባሲና ቆንስላዎችን ለመዝጋት መወሰን የሚኖረው አንድምታ | ባለፈው ረቡዕ ኢትዮጵያ በአልጄሪያ ዋና ከተማዋ አልጀርስ የሚገኘው ኤምባሲዋን ለመዝጋት እንወደሰነችና ከአገሪቱ ጋር የሚኖራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ግን እንደሚቀጥል ኤምባሲው አስታውቋል። በተጨማሪም ኢምባሲው የሚዘጋው እየተካሄደ ባለው ማሻሻያና ከኮቪድ-19 ጋር በተገናኘ እንደሆነም ገልጿል። በአልጀርስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ ካሏት ኢምባሲዎችና ቆንስላዎች መካከል ግማሽ ያህሉን እንደምትዘጋ ካሳወቁ በኋላ በይፋ መዘጋቱ የታወቀ የመጀመሪያው ኤምባሲ ነው። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስት... | https://www.bbc.com/amharic/news-58386457 |
health | በዩኬ የበረራ ሰልጣኝ በወባ ትንኝ ከተነከሰች በኋላ ሕይወቷ ማለፉ በምርመራ ተረጋገጠ | በዩናይትድ ኪንግደም የንግድ አየር መንገድ አውሮፕላን ሰልጣኝ አብራሪ የነበረችው ግለሰብ በወባ ትንኝ ከተነከሰች በኋላ ወደ አንጎል በተሰራጨ ኢንፌክሽን ሳቢያ ሕይወቷ ማለፉ በምርመራ ተረጋገጠ። ነዋሪነቷ ሰፎልክ፣ በሪይ ሴንት ኤድመንድስ የነበረው የ21 ዓመቷ ኦሪያና ፔፐር፣ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር በቤልጂየም፣ አንትወርፕ እያለች በወባ ትንኝ ከተነከሰች ከአምስት ቀናት በኋላ ሕይወቷ ማለፉ ተገልጿል። የሰፎልክ ከፍተኛ የወንጀል መርማሪ የሆኑት ናይጀል ፓርስሊይ፣ ወደፊት ጥሩ ሥራ የሚጠብቃት ወጣት ሞት እጅ... | https://www.bbc.com/amharic/articles/cy7q2xzyp3jo |
business | ሊባኖሳውያን የራሳቸውን ገንዘብ ለማውጣት በባንኮች ላይ የሚፈጽሙት ዘረፋ | በሊባኖስ ለዓመታት በዘለቀው የምጣኔ ሃብት ቀውስ ምክንያት፣ ባንኮች ደንበኞቻቸው በሚያወጡት የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ጥለዋል። ይህ ደግሞ ተጠቃሚዎች ገንዘባቸውን ለማግኘት ኃይል እንዲጠቀሙ እያደረጋቸው ነው። ባለፉት ሳምንታት ዜጎች ካስቀመጡት ገንዘብ የፈለጉትን ያህል ለማውጣት ሽጉጥ ታጥቀወ ወደ ባንኮች በመሄድ ያራሳቸውን ገንዘብ በመሳሪያ በማስገደድ ለማውጣት እየሞከሩ ነው። ይህ ቪዲዮ በዚህ መንገድ ገንዘብ ለማውጣት በሞከሩ ሁለት ሊባኖሳውያን ታሪክ አማካይነት የችግሩን መባባስ ያሳያል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cglg1k2np17o |
health | ኮሮናቫይረስ፡ ድመትና ውሾች ኮቪድ እንደሚይዛቸው ተደረሰበት | የኮቪድ ቫይረስ በለማዳ የቤት ውስጥ እንሰሳት በተለይም በውሾችና በድመቶች ላይ በስፋት እንደሚገኝ አንድ ጥናት አመለከተ። ጥናቱ እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው 196 የኮቪድ ተህዋሲ የጎበኘው ቤተሰብ ላይ ባደረገው ምርምር ነው። በ196 አባወራዎች ላይ በተደረገው ይህ ምርምር 310 ድመቶችና ውሾች የተካተቱበት ነው። ከነዚህ ውስጥ ስድስት ድመቶችና ሰባት ውሾች ተህዋሲውን ተሸክመው ተገኝተዋል። 54ቱ ደግሞ ከዚህ ቀደም ተህዋሲው ይዞ እንደለቀቃቸው የሚያሳይ የበሽታ ተከላካይ ቅንጣት ተገኝቶባቸዋል። ዶ/ር ኤልስ... | https://www.bbc.com/amharic/57662274 |
health | ኮሮናቫይረስ፡ በታንዛኒያ 'የኮቪድ-19 ምልክቶችን ያሳዩ' በርካታ መነኮሳትና ካህናት መሞታቸው ተሰማ | በታንዛኒያ ስድሳ መነኮሳትና 25 ካህናት ባለፉት ሁለት ወራት መሞታቸውን የአገሪቱ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስታወቀች። እነዚህ ካህናትና መነኮሳት የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ታይቶባቸው ነበር ተብሏል። በአገሪቱ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ህሙማን መረጃ ይፋ በማይሆንባት ታንዛኒያ ቤተ ክርስቲያኗ የአገሬው ሰው ከወረርሽኙ እንዲጠነቀቅ ምክሯን ለግሳለች። የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ወረርሽኙን ሲያጣጥሉ የተሰሙ ሲሆን ባለፈው ወር የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ታንዛኒያ ወረርሽኙን ለመከላከል ክትባት የመስጠት ዕቅድ የላትም... | https://www.bbc.com/amharic/news-56272129 |
health | ጃዋር መሐመድ፡ እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናቸው ተገለፀ | የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በትናንት ውሎው በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና 14 ተጠርጣሪዎች የቅድመ ምርመራ መዝገብ ባለፈው ቀጠሮ የተሰጡ ትዕዛዞችን አፈፃፀምና የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ነበር ትናንት፣ ሐሙስ (ነሐሴ 14 2012) ቀጠሮ የያዘው። በትናንትናው ዕለትም ባለፈው ቀጠሮ ተሰጥተው ከነበሩ ትዕዛዞች አንደኛው ተጠርጣሪዎች የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲደረግላቸው የሚል ነበር። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም ከኢትዮጵያ ጤና ኢንስቲትዩት የተላከ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት ማ... | https://www.bbc.com/amharic/53852370 |
health | የአሜሪካ ግዛቶች የኮቪድ-19 ክልከላዎችን ማንሳት ጀመሩ | የቴክሳስ፣ ሚሺጋን፣ ሉዊዚያና እና ሚሲሲፒ ግዛቶች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታ አይሆንም አሉ። የግዛቶቹ አስተዳዳሪዎች ከዚህ ውሳኔ የደረሱት ኮቪድ-19 በአሜሪካ ለአራተኛ ዙር ሊሰራጭ ይችላል የሚል ስጋት ባለበት ወቅት ነው። ሪፓብሊካኑ የቴክሳስ ገዢ ግሬግ አቦት፤ “ቴክሳስን 100% ለመክፈት ጊዜ አሁን ነው” ብለዋል። ቴክሳስ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታ አይደለም በማለት ያወጀች ትልቋ የአሜሪካ ግዛት ነች። በዚህም መሰረት ከአንድ ሳምንት በኋላ የአፍ እና አፍንጫ... | https://www.bbc.com/amharic/news-56262360 |
business | ኢቲ 302 ቦይንግ 737፡ ልክ የዛሬ አንድ ዓመት በኢትዮጵያው አውሮፕላን ላይ ምን ተከሰተ? | ዕሑድ መጋቢት 1 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ለኢትዮጵያዊያን አስደንጋጭ ዕለት ነበር። እርግጥ 'የኢትዮጵያ'' ታሪኩ የከፍታ ነው። የአቪየሽን ኢንዱስትሪው ሲንደፋደፍ 'ET' ከፍ ብሎ በሯል፤ያውም ለዘመናት። በትርፍም፣ በአውሮፕላን ብዛትም፣ በበረራ ስፋትም፣ በመስተንግዶ ጥራትም ሞገስ ተለይቶት አያውቅም። በጥቅሉ ከፍ እንጂ ዝቅ ብሎ አያውቅም። በዚያች ሰንበት ግን 'ማክስ-8' ጎንበስ ካለበት ቀና አልል አለ። አብራሪዎቹ የቻሉትን ሞከሩ። አልሆነም። • ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በመግለጫ ምልልስ እየተወዛገቡ ነው ... | https://www.bbc.com/amharic/news-51797891 |
health | የዝንጀሮ ፈንጣጣ ለኢትዮጵያ ምን ያህል ስጋት ነው? | በአሁኑ ጊዜ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ ቢያንስ በ13 አገራት ከ90 በላይ ሰዎች ላይ መከሰቱ የዓለም ጤና ድርጅት አረጋግጧል። በሽታው በስፋት የታየው በአሜሪካ እና በአውሮፓ አገራት ውስጥ ነው። በንክኪ የሚተላለፈው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ከኮቪድ-19 ጋር ሲነጻጸር የመዛመት ፍጥነቱ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ እንደ ዩናይትድ ኪንግድም ያሉ አገራት "ችላ የምንለው አይደለም" ብለው በልዩ ትኩረት እየሰሩ ነው። ለመሆኑ ይህ በሽታ ኢትዮጵያን ያሳስባታል? በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲቲዩት የበሽታዎች ቅኝት እና ... | https://www.bbc.com/amharic/news-61564071 |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.